Loading
Singer
የዓለም ፡ ፍጻሜ ፡ ምልክቶች የጌታችን ፡ ቃሎች ፡ ትንቢቶቹ ተፈፅመዋል ፡ የሚበዙቱ የምጽአቱ ፡ ቀርቧል ፡ ሰዓቱ አዝ፦ ጌታችን ፡ ኢየሱስ ፡ በታላቅ ፡ ግርማ ፡ በድንገት ፡ ይመጣል በሰማይ ፡ ደመና ፡ ከቅዱሳኑ ፡ ጋር ፡ በክብር ፡ ይገለጣል ፊቱ ፡ ልትቆም ፡ ምን ፡ ያህል (፪x) ፡ ተዘጋጅተሃል ረሃብ ፡ ቸነፈሩ ፡ የምድር ፡ መናወጥ የአህዛብ ፡ ዕውቀት ፡ መከራና ፡ ምጥ ፍጥረቱን ፡ ይዞ ፡ ሲያንገዳግደው የጨለማው ፡ ገዥ ፡ ጨንቆ ፡ ሲያብሰው አዝ፦ ጌታችን ፡ ኢየሱስ ፡ በታላቅ ፡ ግርማ ፡ በድንገት ፡ ይመጣል በሰማይ ፡ ደመና ፡ ከቅዱሳኑ ፡ ጋር ፡ በክብር ፡ ይገለጣል ፊቱ ፡ ልትቆም ፡ ምን ፡ ያህል (፪x) ፡ ተዘጋጅተሃል ሃሰት ፡ አሰራር ፡ ተዓምራቱ የዓለም ፡ ሕዝቦችም ፡ ሲሳሳቱ ዋጋ ፡ ሲያስከፍል ፡ ጌታን ፡ መጥራቱ ቀኑም ፡ ቅርብ ፡ ነው ፡ የድል ፡ ንጋቱ አዝ፦ ጌታችን ፡ ኢየሱስ ፡ በታላቅ ፡ ግርማ ፡ በድንገት ፡ ይመጣል በሰማይ ፡ ደመና ፡ ከቅዱሳኑ ፡ ጋር ፡ በክብር ፡ ይገለጣል ፊቱ ፡ ልትቆም ፡ ምን ፡ ያህል (፪x) ፡ ተዘጋጅተሃል ፍፁም ፡ ባላሰብከው ፡ ሰዓት ፡ ይመጣል ነቅቶ ፡ መጠበቁ ፡ ይሻልሃል በምቾት ፡ ወጥመድ ፡ እንዳትታለል በጸሎት ፡ እየተጋህ ፡ ተጠንቀቅ አዝ፦ ጌታችን ፡ ኢየሱስ ፡ በታላቅ ፡ ግርማ ፡ በድንገት ፡ ይመጣል በሰማይ ፡ ደመና ፡ ከቅዱሳኑ ፡ ጋር ፡ በክብር ፡ ይገለጣል ፊቱ ፡ ልትቆም ፡ ምን ፡ ያህል (፪x) ፡ ተዘጋጅተሃል ወንጌል ፡ ታውጆ ፡ የዘለዓለም ሰዎች ፡ አምልጠው ፡ ከጥፋት ፡ ዓለም የተባረከ ፡ ተስፋችን ፡ ኢየሱስ ክፉን ፡ ደምስሶ ፡ በድል ፡ ሊነግስ አዝ፦ ጌታችን ፡ ኢየሱስ ፡ በታላቅ ፡ ግርማ ፡ በድንገት ፡ ይመጣል በሰማይ ፡ ደመና ፡ ከቅዱሳኑ ፡ ጋር ፡ በክብር ፡ ይገለጣል ፊቱ ፡ ልትቆም ፡ ምን ፡ ያህል (፪x) ፡ ተዘጋጅተሃል