Loading
Singer
በደልን ፡ ይቅር ፡ የሚል ፡ አመጻን ፡ የሚያሳልፍ ከጥፋት ፡ ሊያድናቸው ፡ በሕዝቡ ፡ ላይ ፡የሚሰፍፍ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ አምላክ ፡ ማነው ፡ ምህረቱ ፡ የበዛ? ቅዱሳንህ ፡ ሲሰደዱ ፡ መከራውም ፡ ሲበዛ አዝ፦ ርስትህን ፡ ለማላገጫ ፡ አሳልፈህ ፡ አትስጥ የተቀደሰ ፡ መቅደስህን ፡ በጠላት ፡ አታስረግጥ የእግዚአብሔር ፡ ዕድል ፡ ፈንታ ፡ተፅፏል ፡ ህዝቡ ፡ ነው ! ሊያመልከው ፡ ሊያገለግለው ፡ ከግብጽ ፡ አገር ፡ ያፈለሰው አርነቱን ፡ በባርነት ፡ ሊተካ ፡ የሚከጅለው "ይገባኛል " ፡ የሚል ፡ ማነው ? ሕዝቡ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው! አዝ፦ ርስትህን ፡ ለማላገጫ ፡ አሳልፈህ ፡ አትስጥ የተቀደሰ ፡ መቅደስህን ፡ በጠላት ፡ አታስረግጥ እስከዛሬ ፡ከብረሃል ፡ በአህዛብ ፡ ተፈርተሃል የጠላትን ፡ እርግማን ፡ በረከት ፡ አድርገሃል የአሳዳጁን ፡ ፈረሶች ፡ በባሕር ፡ አስጥመሃል በክንድህ ፡ ተከላክለህ ፡ ርስትህን ፡ ጠብቀሃል አዝ፦ ርስትህን ፡ ለማላገጫ ፡ አሳልፈህ ፡ አትስጥ የተቀደሰ ፡ መቅደስህን ፡ በጠላት ፡ አታስረግጥ (፪x)