Loading
Singer
Updated 9/8/2026
አዝ፦ በድል ፡ በድል (፪x) እያሳለፈኝ ፡ ቆምኩ ፡ በተዓምር እያስመለጠኝ ፡ በቸርነቱ ያዘምረኛል ፡ ይህ ፡ ቸር ፡ አቤቱ (፪x) አቤቱ ፡ አቤቱ ፡ በዛ ፡ ቸርነቱ (፬x) ጠላቶች ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ሲማማሉ የሚረዳው ፡ የታል ፡ ሲሉ (፪x) ረዳቴ ፡ ከሰማይ ፡ ወረደልኝ አለሁልህ ፡ ልጄ ፡ እያለኝ አለሁልህ ፡ ልጄ ፡ እያለኝ (፪x) በፍቅርህ ፡ ብዛት ፡ በቸርነትህ እኔስ ፡ አለፍኩኝ ፡ በአባትነትህ ለነገ ፡ ደግሞ ፡ ዋስትናዬ ፡ ነህ ስጋት ፡ አይገባኝ ፡ ጌታዬ ፡ በአንተ (፪x) አዝ፦ በድል ፡ በድል (፪x) እያሳለፈኝ ፡ ቆምኩ ፡ በተዓምር እያስመለጠኝ ፡ በቸርነቱ ያዘምረኛል ፡ ይህ ፡ ቸር ፡ አቤቱ (፪x) አቤቱ ፡ አቤቱ ፡ በዛ ፡ ቸርነቱ (፬x) ከአስፈሪው ፡ መንገዴ ፡ ታደከኝ በእጆችህ ፡ ይዘኸኝ (፪x) ወጥመድ ፡ ተሰበረ ፡ አመለጥኩኝ በእጆችህ ፡ ይዘኸኝ በእጆችህ ፡ ይዘኸኝ (፪x) በፍቅርህ ፡ ብዛት ፡ በቸርነትህ እኔስ ፡ አለፍኩኝ ፡ በአባትነትህ ለነገ ፡ ደግሞ ፡ ዋስትናዬ ፡ ነህ ስጋት ፡ አይገባኝ ፡ ጌታዬ ፡ በአንተ (፪x)