Loading
Singer
አዝ፦ ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ተገልጦ ፡ ስትሰራ ፡ አይቻለሁ ከእኔ ፡ ምለው ፡ የለም ፡ የሆነው ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ነው ላከብርህ ፡ ዘንድ ፡ ይገባኛል ፡ ቸሩ ፡ አባቴ ፊትህ ፡ ወድቄ ፡ ተንበርክኬ ፡ በጉልበቴ ዝቅ ፡ ብዬ ፡ ላክብርህ ታይብኝ ፡ ከፍ ፡ ብለህ (፪x) እንደልጅ ፡ አይተኸኝ ፡ በልጅነት ፡ ወራት ክፉ ፡ አመሌን ፡ ቻልከው ፡ የምህረትህ ፡ ብዛት አልጨከንክብኝም ፡ እንድሰጥ ፡ ታልፌ ስንቶችን ፡ ከመንገድ ፡ ካስቀረው ፡ ተርፌ አለሁ ፡ በገናዬን ፡ ዛሬም ፡ አልሰቀልኩም ስለቸርነትህ/ስለደግነትህ ፡ መዘመር ፡ አልተውኩን (፪x) አያምርብኝም ፡ በእኔ ፡ ስንፍና ፡ ጌታ ፡ ውለታህ ፡ ብዙ ፡ ነውና አያምርብኝም ፡ በእኔ ፡ ስንፍና ፡ ኢየሱስ ፡ ውለታህ ፡ ብዙ ፡ ነውና (፪x) አዝ፦ ኃይልህ ፡ በድካሜ ፡ ተገልጦ ፡ ስትሰራ ፡ አይቻለሁ ከእኔ ፡ ምለው ፡ የለም ፡ የሆነው ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ነው ላከብርህ ፡ ዘንድ ፡ ይገባኛል ፡ ቸሩ ፡ አባቴ ፊትህ ፡ ወድቄ ፡ ተንበርክኬ ፡ በጉልበቴ ዝቅ ፡ ብዬ ፡ ላክብርህ ታይብኝ ፡ ከፍ ፡ ብለህ (፪x) በውድቀቴ ፡ ስቀህ ፡ ጀርባ ፡ አልሰጠኸኝም ዓይንህም ፡ እንዳየች ፡ አልበየንክብኝም ይልቅ ፡ አስጠጋኸኝ ፡ መከርከኝ ፡ ለልቤ ከቶ ፡ እንደማይበጅ ፡ ሰውኛው ፡ ሃሳቤ ለተፍገመገመው ፡ ኃይልን ፡ የሰጠኸው የሳተውን ፡ ደግሞ ፡ ቀርበህ ፡ የመለስከው የእንደገና ፡ አምላክ ፡ አደረከኝ ፡ ቀና ሃፍረቴን ፡ ሸፍነህ ፡ የቤቴን ፡ ገበና አያምርብኝም ፡ በእኔ ፡ ስንፍና ፡ ጌታ ፡ ውለታህ ፡ ብዙ ፡ ነውና አያምርብኝም ፡ በእኔ ፡ ስንፍና ፡ ኢየሱስ ፡ ውለታህ ፡ ብዙ ፡ ነውና (፪x)