Loading
Singer
በጨነቀኝ ፡ ጊዜ ፡ ፀሎቴ በእንባ ፡ ስነግርህ ፡ ጭንቀቴን ለካስ ፡ ሰምተኸኛል ፡ ተመሥገን ነዶ ፡ አስታቀፍከኝ ፡ ያማረውን አዝ፦ በዚያ ፡ በጣር ፡ ጊዜ ፡ ለሰማኸኝ በሄድኩበት ፡ ሁሉ ፡ ለመራኸኝ ይሰዋ ፡ በፊትህ ፡ ምሥጋናዬ ሰምሮልኝ ፡ አየሁኝ ፡ በአንተ ፡ ኑሮዬ (፪x) ሰምሮልኝ ፡ አየሁኝ ፡ በአንተ ፡ ኑሮዬ (፬x) ሁሉ ፡ አልፎ ፡ ዛሬ ፡ ዘምራለሁ የቃርሚያውን ፡ ሕይወት ፡ አልፌያለሁ እልፍ ፡ አደረገኝ ፡ አከበረኝ በአምላኬ ፡ ከፍታን ፡ አገኘሁኝ አዝ፦ በዚያ ፡ በጣር ፡ ጊዜ ፡ ለሰማኸኝ በሄድኩበት ፡ ሁሉ ፡ ለመራኸኝ ይሰዋ ፡ በፊትህ ፡ ምሥጋናዬ ሰምሮልኝ ፡ አየሁኝ ፡ በአንተ ፡ ኑሮዬ (፪x) እንደመሸ ፡ አልቀረም ፡ ነግቶልኛል ከአምላኬ ፡ ጉብኝት ፡ ሆኖልኛል የጨለማው ፡ ዘመን ፡ አለፈና ልዘምር ፡ በቃሁኝ ፡ አልኩኝ ፡ ቀና አዝ፦ በዚያ ፡ በጣር ፡ ጊዜ ፡ ለሰማኸኝ በሄድኩበት ፡ ሁሉ ፡ ለመራኸኝ ይሰዋ ፡ በፊትህ ፡ ምሥጋናዬ ሰምሮልኝ ፡ አየሁኝ ፡ በአንተ ፡ ኑሮዬ (፪x)