Loading
Singer
በማስተዋል ፡ አደርጋለሁ እረኛዬን ፡ እሰማዋለሁ ያውቃል ፡ ከእኔ ፡ በብዙ ፡ ሺህ ነፍሴ ፡ ይምራሽ ፡ አምላክሺ ቀድሞ ፡ አይቶ ፡ የእኔን ፡ መንገድ መራኝ ፡ በድንቅ ፡ በእርሱ ፡ ፈቃድ ግራ ፡ ቀኜን ፡ ስላየልኝ ተማምኜ ፡ እወጣለሁኝ አዝ፦ በችኮላ ፡ ከቶ ፡ አልወጣም በመኮብለል ፡ ደግሞ ፡ አልሄድም እግዚአብሔር ፡ ይቀድመኛል በፈቃዱ ፡ ይመራኛል (፪x) በድንኳኔ ፡ እጠብቃለሁ የአንተን ፡ ትእዛዝ ፡ እሰማለሁ ውጣ ፡ ካልከኝ ፡ እወጣለሁ ጠላቶቼን ፡ እመታለሁ ጠላት ፡ ለእኔ ፡ ለሚያስበው ግድም ፡ አይለኝ ፡ ስለሚለው የእግዚአብሔር ፡ ኃይል ፡ ሸፍኖኛል ደሙ ፡ እርሱ ፡ እኔን ፡ ስቦኛል አዝ፦ በችኮላ ፡ ከቶ ፡ አልወጣም በመኮብለል ፡ ደግሞ ፡ አልሄድም እግዚአብሔር ፡ ይቀድመኛል በፈቃዱ ፡ ይመራኛል (፪x)