Loading
Singer
አዝ፦ በችግር ፡ ጓደኛ ፡ በመከራ አብሮኝ ፡ የሚሰቃይ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ በታናሽነቴ ፡ የማይንቀኝ ዘመድ ፡ አግኝቻለሁ ፡ የሚወደኝ (፪x) ኢየሱስ ፡ የሚባል ፡ ድንቅ ፡ መካር የሰላም ፡ አለቃ ፡ ደግሞም ፡ ፍቅር የሚባል ፡ ጓደኛ ፡ አግኝቻለሁ እኔም ፡ በእርሱ ፡ ሰላም ፡ ረክቻለሁ አዝ፦ በችግር ፡ ጓደኛ ፡ በመከራ አብሮኝ ፡ የሚሰቃይ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ በታናሽነቴ ፡ የማይንቀኝ ዘመድ ፡ አግኝቻለሁ ፡ የሚወደኝ (፪x) ችግሬን ፡ በሙሉ ፡ ወስዶት ፡ እርሱ ደስታን ፡ ለእኔ ፡ ሰጠኝ ፡ ከመንፈሱ ሃዘን ፡ ስወርድ ፡ አብሮኝ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ስደሰትም ፡ አብሮኝ ፡ በተራራ አዝ፦ በችግር ፡ ጓደኛ ፡ በመከራ አብሮኝ ፡ የሚሰቃይ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ በታናሽነቴ ፡ የማይንቀኝ ዘመድ ፡ አግኝቻለሁ ፡ የሚወደኝ (፪x) ለነፍሱ ፡ ሳይሳሳ ፡ የሞተልኝ እጅግ ፡ በጣም ፡ አድርጐ ፡ የሚወደኝ አባት ፡ አግኝቻለሁ ፡ የማይተወኝ እስከ ፡ ለዘለዓለም ፡ የሚመራኝ አዝ፦ በችግር ፡ ጓደኛ ፡ በመከራ አብሮኝ ፡ የሚሰቃይ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ በታናሽነቴ ፡ የማይንቀኝ ዘመድ ፡ አግኝቻለሁ ፡ የሚወደኝ (፪x)