Loading
የታል እስኪ የታል በስራ ሚበልጠው እስኪ ይነሳ የታል የታል እስኪ የታል በዝና ሚበልጠው እስኪ ይነሳ የታል ጌታ እኩያ የለህም አንተ መተኪያ የለህም ዙፋን ላይ ብቻውን በሰማይ ብቻውን ግዛቱ ብቻውን ስልጣኑ ብቻውን ብቻውን እርሱ ብቻውን/4 ለየት ያለ ጌታ አቻ ያልተገኘለት የሰማይ የምድሩ ፈጠራ ባለቤት እርሱ በፈጠረው መቼ ሌላ ያዛል መልክ መልክ አሲዞ ያሻውን ያረጋላ ያረጋላ ብቻውን ያረገዋል ያረጋላ እየስይስ ያረገዋል ይችላህ ብቻውን ይችላዋል ይችላህ አምላኬ ይችላዋል ሲሰለፍ ብቻውን ሲዋጋ ብቻውን ሲረታ ብቻውን ሲያሸንፍ ብቻውን ብቻውን እርሱ ብቻውን/4 እንዳንተ እንዳንተ ጌታ ማን አለ ሁሉን የረታ እንዳንተ እንዳንተ እየሱስ ማን አለ የፀና ንጉስ የታል እስኪ የታል በስራ ሚበልጠው እስኪ ይነሳ የታል የታል እስኪ የታል በዝና ሚበልጠው እስኪ ይነሳ የታል ጌታ እኩያ የለህም አንተ መተኪያ የለህም ሲሰራ ባይገባ እንዴት አይባልም እርሱ ይመርምር እንጂ አይመረመርም ምድርን ሲሞላ ሰማይን ሲያፀና ያማከረው የለም ብቻውን ገናና ገናና ብቻውን ገናና ነው ገናና ንጉሴ ገናና ነው ገናና ብቻውን ገናና ነው ገናና እየሱስ ገናና ነው
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.