Loading
Singer
አዝ፦ ብቻውን ፡ ተዋግቶ ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ የእኛ ፡ ነው ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ የእኛ ፡ ነው ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ ታዲያ ፡ የምንፈራው ፡ ለምንድ ፡ ነው? (፪x) የሰልፉ ፡ ባለቤት ፡ እግዚአብሔር እንደ ፡ አህዛብ ፡ አማልክት ፡ ማይቀያየር ባሪያዎቹን ፡ ከእሳት ፡ ውስጥ ፡ ያወጣል በኃይሉ ፡ ከፍ ፡ ያለውን ፡ ያደርጋል (፪x) አዝ፦ ብቻውን ፡ ተዋግቶ ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ የእኛ ፡ ነው ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ የእኛ ፡ ነው ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ ታዲያ ፡ የምንፈራው ፡ ለምንድ ፡ ነው? (፪x) በሰው ዓይን ፡ ሲታዩ ፡ አስፈሪዎች በእግዚአብሔር ፡ ፊት ፡ ግን ፡ እጅግ ፡ ቀላለሎች ጥላቸው ፡ ተገፏል ፡ ልባችን ፡ አይፍራ ነገ ፡ ይሆኑልናል ፡ እንደ ፡ እንጀራ (፪x) አዝ፦ ብቻውን ፡ ተዋግቶ ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ የእኛ ፡ ነው ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ የእኛ ፡ ነው ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ ታዲያ ፡ የምንፈራው ፡ ለምንድ ፡ ነው? (፪x) ድል ለተነሳው ፡ ለጠላት ፡ ዛቻ ለሚያስፈራራን ፡ በወሬ ፡ ብቻ እጅ ፡ አንሰጥም ፡ ነገሩ ፡ ይገለበጣል የእግዚአብሔር ፡ ሐሳብ ፡ ይፈጸማል (፪x) አዝ፦ ብቻውን ፡ ተዋግቶ ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ የእኛ ፡ ነው ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ የእኛ ፡ ነው ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ ታዲያ ፡ የምንፈራው ፡ ለምንድ ፡ ነው? (፪x) ሁኔታዎችን ፡ አይቶ ፡ ተስፋ ፡ መቁረጥ ወየሁ ፡ ጠፋሁ ፡ እያሉ ፡ መደናገጥ አይሆንም ፡ ከእንግዲህ ፡ አባት ፡ አለን በእርሱ ፡ ከአሸናፊዎች ፡ እንበልጣለን (፪x) አዝ፦ ብቻውን ፡ ተዋግቶ ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ የእኛ ፡ ነው ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ የእኛ ፡ ነው ፡ የሚያሸንፍ ፡ አምላክ ታዲያ ፡ የምንፈራው ፡ ለምንድ ፡ ነው? (፪x) ዘጸ. 15፡3 ‹‹እግዚአብሔር ፡ ተወጊ ፡ ነው ፡ ስሙም… ›› [1] ዘጸ. 14፡14 ‹‹እግዚአብሔር ፡ ስለ ፡ እናንተ ፡ ይዋጋል …›› [2]