Loading
Singer
አንደበት ፡ ኖሯቸው ፡ ምድርና ፡ ሰማይ ምነው ፡ ቢናገሩ ፡ እንደሌለው ፡ መሳይ (፫x) እኔስ ፡ በዚች ፡ ቃሌ ፡ በትንሿ ፡ አንደበት አልወጣልህ ፡ አለኝ ፡ ዘምሬ ፡ የእርሱን ፡ ምህረት ያምላኬን ፡ በጐነት (አሃሃ) ፡ የአምላኬን ፡ ቸርነት ጥሩ ፡ ቃል ፡ ተመርጦ ፡ ዜማ ፡ ቢደረደር በመልካም ፡ አዋቂ ፡ አምሮ ፡ ቢቀናበር ልሳን ፡ ያለው ፡ ሁሉ ፡ ለአፍታ ፡ ሳያባራ አይበቃም ፡ ቢዘመር ፡ ስለእርሱ ፡ ቢወራ (፪x) አዝ፦ (አሃሃ) ፡ ብቻውን ፡ ጌታ ፡ ነው ፤ (አሃሃ) ፡ መለኪያ ፡ የለውም (አሃሃ) ፡ ፍጥረት ፡ ይራመዳል ፤ (አሃሃ) ፡ እርሱ ፡ እንደሚለው (አሃሃ) ፡ ይገድላል ፡ ያድናል ፤ (አሃሃ) ፡ ይሾማል ፡ ይሽራል (አሃሃ) ፡ ዐይኖቹን ፡ እይታ ፤ (አሃሃ) ፡ ማን ፡ ሸሽቶ ፡ ይሰወራል ሄይ (፮x) ፡ ጌታ ፡ ነህ ፡ ብንለው ሄይ (፮x) ፡ ሲችል ፡ ስላየነው ሄይ (፮x) ፡ ኤልሻዳይ ፡ ብንለው ሄይ (፮x) ፡ ሲችል ፡ ስላየነው አስፈሪው ፡ ማዕበል ፡ ወጀብ ፡ ታዘዘለት ተራራው ፡ ለክብሩ ፡ ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ አለለት ብቻውን ፡ ኤልሻዳይ ፡ በሃይል ፡ ይገዛል ቢወድም ፡ ባይወድም ፡ ፍጥረት ፡ ይታዘዛል (፪x) ሄይ (፮x) ፡ ጌታ ፡ ነህ ፡ ብንለው ሄይ (፮x) ፡ ሲችል ፡ ስላየነው ሄይ (፮x) ፡ ኤልሻዳይ ፡ ብንለው ሄይ (፮x) ፡ ሲችል ፡ ስላየነው check this section again አጥቢያ ፡ ኮከብ ፡ ቆመው ፡ ፊቱ ፡ ሲዘምሩ ሰማያት ፡ ሲሰግዱ ፡ ሲሞሉ ፡ በክብሩ (፫x) መስፈሪያም ፡ ሲለካ ፡ ዙሪያዋን ፡ ሲገምት ማን ፡ ነበር ፡ ያገዘው ፡ ምድርን ፡ ሲመሰርት (፫x) በአደባባዮች ፡ ላይ ፡ ክህደት ፡ ሲዘመር ያወቀ ፡ ሲመስለው ፡ ሰው ፡ ብዙ ፡ ሲናገር የለም ፡ ያሉት ፡ ሄዱ ፡ ከነኮተታቸው የእኛ ፡ አምላክ ፡ ግን ፡ አለ ፡ በዙፋኑ ፡ ይኸው (፪x) አዝ፦ (አሃሃ) ፡ ብቻውን ፡ ጌታ ፡ ነው ፤ (አሃሃ) ፡ መለኪያ ፡ የለውም (አሃሃ) ፡ ፍጥረት ፡ ይራመዳል ፤ (አሃሃ) ፡ እርሱ ፡ እንደሚለው (አሃሃ) ፡ ይገድላል ፡ ያድናል ፤ (አሃሃ) ፡ ይሾማል ፡ ይሽራል (አሃሃ) ፡ ዐይኖቹን ፡ እይታ ፤ (አሃሃ) ፡ ማን ፡ ሸሽቶ ፡ ይሰወራል ሄይ (፮x) ፡ ጌታ ፡ ነህ ፡ ብንለው ሄይ (፮x) ፡ ሲችል ፡ ስላየነው ሄይ (፮x) ፡ ኤልሻዳይ ፡ ብንለው ሄይ (፮x) ፡ ሲችል ፡ ስላየነው