Loading
Singer
አንደበት ፡ ይታክታል የሆድን ፡ ሁሉ ፡ ቢናገር ለመጣው ፡ ለሄደው ፡ ሁሉ የሚያልፍበትን ፡ ቢዘረዝር የሰሚም- ፡ የሰሚም ፡ ጆሮ ፡ ይዝላል ለጊዜው ፡ ለሰሞንም ፡ ቢያዝን ብቻ ፡ ልቤን ፡ ደግፈው አልፈዋለው ፡ ብርቱውን ፡ ቀን ብቻ ፡ ልቤን ፡ ደግፈው አልፈዋለሁ ፡ ክፍውን ፡ ቀን እጠራሃለሁ በስምህ ፡ ውስጥ ፡ ሰላም ፡ አለ እጠራሃለሁ በስምህ ፡ ውስጥ ፡ ብርታት ፡ አለ በስምህ ፡ ውስጥ እግዚአብሔር አዝ፦ በሥምህ ፡ ውስጥ ፡ ሰላም ፡ አለ በሥምህ ፡ ውስጥ ፡ እረፍት ፡ አለ በሥምህ ፡ ውስጥ ፡ ጽናት ፡ አለ በሥምህ ፡ ውስጥ ከፀሓይ ፡ በታች ፡ መልስ ፡ ባጣሁለት ፡ ጉዳይ ቢያይልም ፡ ግርታዬ ፡ አይኔን ፡ ተክያልህ ፡ ሰማይ ከያዘኝ ፡ ከከበበኝ ፡ በላም ፡ አንተን ፡ አምንሃለሁ ብቻ ፡ ልቤን ፡ ደግፈው አልፈዋለው ፡ ብርቱውን ፡ ቀን ብቻ ፡ ልቤን ፡ ደግፈው አልፈዋለሁ ፡ ክፍውን ፡ ቀን ልቤ ፡ ተጠብቆ ፡ በሚሆነው ፡ ነገር እታገስሃለሁ ፡ አለህ ፡ አንድ ፡ ነገር ብቻ ፡ ልቤን ፡ ጠብቀው አልፈዋለው ፡ ብርቱውን ፡ ቀን ብቻ ፡ ልቤን ፡ ደግፈው አልፈዋለሁ ፡ ክፍውን ፡ ቀን አዝ፦ በሥምህ ፡ ውስጥ ፡ ሰላም ፡ አለ በሥምህ ፡ ውስጥ ፡ እረፍት ፡ አለ በሥምህ ፡ ውስጥ ፡ ጽናት ፡ አለ በሥምህ ፡ ውስጥ ልብ ፡ ብቻውን ፡ ሲቀር ፡ በሃሳብ ፡ ሲወረር በሁነኛ ፡ ነፋስ ፡ በማዕበል ፡ ሲሰወር ደጋፊ ፡ ከሌለው ፡ ማን ፡ ከማን ፡ ያስጣል ልብ ፡ የወደቀ ፡ ቀን ፡ ለሞት ፡ እጅ ፡ ያሰጣል ልቤን ፡ የሚታደግ ፡ ብርቱ ፡ ግንብ ፡ አለቴ አጥር ፡ ሃይሌ ፡ ስምህ ፡ ነው ፡ የተስፋ ፡ ጽናቴ አንተ ፡ ነህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጽኑ ፡ መታመኛ አደራ ፡ የምለው ፡ አንተን ፡ ነው ፡ የልቤን ፡ መገኛ አዝ፦ በሥምህ ፡ ውስጥ ፡ ሰላም ፡ አለ በሥምህ ፡ ውስጥ ፡ እረፍት ፡ አለ በሥምህ ፡ ውስጥ ፡ ጽናት ፡ አለ በሥምህ ፡ ውስጥ