Loading
Singer
ሠማዩ ፡ የአንተ ፡ ነው ፣ የአንተ ፡ ነው ምድሩ ፡ የአንተ ፡ ነው ፣ የአንተ ፡ ነው (፪x) ባለጠግነትህ ፡ ዓለምን ፡ ሸፈነው (፬x) በበረከት ፡ የሚኖር ፡ ግርማው ፡ የሚያስፈራ ድህነትን ፡ የማያውቅ ፡ ችግር ፡ የማይፈራ በዘመናት ፡ መሃከል ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ያለ ፡ ማነው ባለጠጋ ፡ መሆንክህን ፡ እኔ ፡ እናገራለሁ (፪x) ባለጠግነትህ ፡ ዓለምን ፡ ሸፈነው (፬x) የእኔ ፡ አምላክ ፡ ክብር ፡ ያለዉ ፡ ክብር ፡ ያለው አምላኬ ፡ ሞገስ ፡ ያለው ፡ ሞገስ ፡ ያለዉ (፪x) ክብር ፡ ያለው ፡ ሞገስ ፡ ያለዉ ሁሉም ፡ ያለው (፬x) ባለጠግነትህ ፡ ዓለምን ፡ ሸፈነው (፬x) ባህሪህ ፡ መልካም ፡ ነው ግሩም ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው አንተን ፡ ተመልክቶ ፡ እማይወድ ፡ ማነው አቤት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፣ አቤት ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፬x)