Loading
Singer
አዝ፦ በአዝመራ ፡ ጊዜ ፡ መኝታ ፡ በጽሞና ፡ ጊዜ ፡ ጫጫታ የሰልፍ ፡ ነው ፡ የድል ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ እልልታ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ማስተዋልን ፡ ስጠን ፡ ጊዜ ፡ እንዳያመልጠን መከራው ፡ እግሩን ፡ ከማውጣቱ ፡ አቆምን ፡ መንበርከክ ፡ በፊቱ የጸሎት ፡ መሰዊያ ፡ አፈረስን ፡ መስሎናል ፡ ሰማይ ፡ የደረስን የምድረበዳው ፡ ትውልድ ፡ በውነ ፡ በወጉ ፡ አያውቅም ፡ ፡ ጦርነት መሬትን ፡ አልረገጠም ፡ በእግሩ ፡ አታሎት ፡ እሩጫው ፡ ግርግሩ አዝ፦ በአዝመራ ፡ ጊዜ ፡ መኝታ ፡ በጽሞና ፡ ጊዜ ፡ ጫጫታ የሰልፍ ፡ ነው ፡ የድል ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ እልልታ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ማስተዋልን ፡ ስጠን ፡ ጊዜ ፡ እንዳያመልጠን እርስ ፡ በርስ ፡ እየተሟሟቅን ፡ ነፍሳትን ፡ ተዘርፈን ፡ አለቅን መርከቡ ፡ መልህቁን ፡ ዘርግቶ ፡ ይጣራል ፡ ተሳፋሪ ፡ ጠፍቶ ይቺ ፡ አለም ፡ ካልደረስንላት ፡ ጨውና ፡ ብርሀን ፡ የላት ህመሟ ፡ ሄደ ፡ እየቀጠለ ፡ መድሀኒት ፡ በእጃችን ፡ አለ አዝ፦ በአዝመራ ፡ ጊዜ ፡ መኝታ ፡ በጽሞና ፡ ጊዜ ፡ ጫጫታ የሰልፍ ፡ ነው ፡ የድል ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ እልልታ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ማስተዋልን ፡ ስጠን ፡ ጊዜ ፡ እንዳያመልጠን ተባባልን ፡ እኔ ፡ ካንተ ፡ አላንስም ፡ ታወቅን ፡ ጌታ ፡ ባልሰጠን ፡ ሥም ተራራቅን ፡ አጥር ፡ እያጠበቅን ፡ ለፍቅር ፡ ክፍያ ፡ ጠየቅን በእልህ ፡ ሳይሰፋ ፡ ገደሉ ፡ ለበደልን ፡ ላጎደልነው ፡ ሁሉ ንስሀ ፡ እንገባለን ፡ ፊትህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ይምጣልን ፡ ምህረትህ