Loading
Singer
በአለንጋ ፡ አልገታኝም ፡ የበረት ፡ ዘንግ ፡ ይዞ አላስማረከኝም ፡ ሰይፉን ፡ በኔ ፡ መዝዞ (፪x) ከዚህ ፡ በሚበልጥ ፡ ኃይል ፡ በፍቅሩ ፡ ጎበኘኝ ጉልበቴን ፡ አስገዛ ፡ መስቀሉን ፡ ሊያሳየኝ (፪x) አዝ:- ሃሌ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ (፫x) መስቀልህ ፡ አወጀው ፡ ነፃነቴን ቃልህም ፡ አጸናው ፡ መሠረቴን መከራ ፡ ስቧጥጥ ፡ ጉዞ ፡ ሲከብድብኝ ተንሸራትቼ ፡ እንድወድቅ ፡ ከስር ፡ ሲናድብኝ (፪x) የድል ፡ ቀን ፡ ቢነጋ ፡ ኢየሱስ ፡ ሞተና በጠላት ፡ ተጫማሁ ፡ ኃይል ፡ አገኘሁና (፪x) አዝ:- ሃሌ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ (፫x) መስቀልህ ፡ አወጀው ፡ ነፃነቴን ቃልህም ፡ አጸናው ፡ መሠረቴን ከጐንህ ፡ ፈስሶልኝ ፡ ፍቅርህን ፡ ጠጥቻለሁ ከተበሳው ፡ እጅህ ፡ ሆዴን ፡ ሞልቻለሁ (፪x) የእግሮችህ ፡ ቀዳዶች ፡ ያጫሙኝ ፡ ጠላት ፡ ላይ የራስህ ፡ ላይ ፡ እሾህ ፡ ሆነኝ ፡ ክብርህን ፡ እንዳይ (፪x) አዝ:- ሃሌ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ (፫x) መስቀልህ ፡ አወጀው ፡ ነፃነቴን ቃልህም ፡ አጸናው ፡ መሠረቴን ኑሮዬ ፡ ይገባሃል ፡ አንተ ፡ ሚስጥረኛዬ የነፍሴ ፡ ፍላጎት ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ጌታዬ (፪x) ጠላት ፡ አደናግጦ ፡ ልክድህ ፡ ሲያባብለኝ ያንተን ፡ ጣራ ፡ አስቤ ፡ እንድመለስ ፡ እርዳኝ (፪x) አዝ:- ሃሌ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ (፫x) መስቀልህ ፡ አወጀው ፡ ነፃነቴን ቃልህም ፡ አጸናው ፡ መሠረቴን