Loading
Singer
በዓለም ፡ ተጥዬ ፡ ዋጋም ፡ ሳይኖረኝ በሰውም ፡ ተንቄ ፡ ስፍራንም ፡ ሳላገኝ ቃሉን ፡ ሲያወጣ ፡ ከማደሪያው ፡ ቦታ ታላቅም ፡ ሠራዊት ፡ አድርጐኛል ፡ ጌታ (፪x) ሕይወቴን ፡ ሊጐዳ ፡ ዝቶብኝ ፡ ጠላቴ እግዚአብሔር ፡ አዳነኝ ፡ ጥሶ ፡ ገብቶ ፡ ቤቴ እኔም ፡ አመልካለሁ ፡ ይህን ፡ ታላቅ ፡ ጌታ አውጥቶኛልና ፡ ከጭንቅ ፡ ከመከራ አዝ፦ የውለታው ፡ ብዛት ፡ ሳስብ ፡ ይገርመኛል ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገው ፡ እጅግ ፡ ይደንቀኛል (፪x) ምኔን ፡ አይተህ ፡ ልበል ምኔ ፡ ስቦት ፡ ይሆን ፡ እንዲህ ፡ የወደደኝ እንዲሁ ፡ በፍቅሩ ፡ የእራሱ ፡ አደረገኝ ከጠላት ፡ መንጋጋ ፡ ፈልቅቆ ፡ አስመለጠኝ ከዓለም ፡ ለይቶ ፡ ለእራሱ ፡ አደረገኝ አይተወኝም ፡ እርሱ ፡ መቼም ፡ አይረሳኝም በፍቅሩ ፡ እኔን ፡ ገዝቶ ፡ ልቤን ፡ ማርኮ አምነዋለሁ ፡ እርሱን ፡ ዘለዓለማዊ ፡ ነው አይጥለኝም ፡ ሁሌ ፡ ታማኝ ፡ ወዳጄ ፡ ነው አዝ፦ የውለታው ፡ ብዛት ፡ ሳስብ ፡ ይገርመኛል ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገው ፡ እጅግ ፡ ይደንቀኛል (፪x) ምኔን ፡ አይተህ ፡ ልበል ምኔ ፡ ስቦት ፡ ይሆን ፡ እንዲህ ፡ የወደደኝ እንዲሁ ፡ በፍቅሩ ፡ የእራሱ ፡ አደረገኝ ከጠላት ፡ መንጋጋ ፡ ፈልቅቆ ፡ አስመለጠኝ ከዓለም ፡ ለይቶ ፡ ለእራሱ ፡ አደረገኝ ደግፎ ፡ ያቆመኝ ፡ እኔን ፡ በምህረት የማውቀው ፡ ጌታን ፡ ነው ፡ ደግሞም ፡ በቸርነት መጣ ፡ እኔንም ፡ አይቶ ፡ ያነሳኝ ፡ እርሱ ፡ ነው ዛሬም ፡ ቢሆን ፡ ነገ ፡ በእርሱ ፡ እታመናለሁ አዝ፦ የውለታው ፡ ብዛት ፡ ሳስብ ፡ ይገርመኛል ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገው ፡ እጅግ ፡ ይደንቀኛል (፪x) ምኔን ፡ አይተህ ፡ ልበል ምኔ ፡ ስቦት ፡ ይሆን ፡ እንዲህ ፡ የወደደኝ እንዲሁ ፡ በፍቅሩ ፡ የእራሱ ፡ አደረገኝ ከጠላት ፡ መንጋጋ ፡ ፈልቅቆ ፡ አስመለጠኝ ከዓለም ፡ ለይቶ ፡ ለእራሱ ፡ አደረገኝ