Loading
Singer
አዝ፦ በዓለም ፡ ከሚገኝ ፡ ብዙ ፡ ክብር ፡ ይልቅ ስለ ፡ ክርስቶስ ፡ መነቀፍን ፡ የሚበልጥ ብድራቱን ፡ ትኩር ፡ ብሎ ፡ አይቷልና ሙሴ ፡ ጌታን ፡ አከበረው ፡ በሕይወት ፡ ጐዳና ለጊዜው ፡ በኀጢአት ፡ ከሚገኝ ፡ ደስታ ፡ ይልቅ ለጌታ ፡ መነቀፍ ፡ እጅግ ፡ እንደሚበልጥ ታውቆት ፡ ክብሩን ፡ ተወ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ተማምኖ ጌታም ፡ አልተወውም ፡ አየሁ ፡ ልጄ ፡ ብሎ አዝ፦ በዓለም ፡ ከሚገኝ ፡ ብዙ ፡ ክብር ፡ ይልቅ ስለ ፡ ክርስቶስ ፡ መነቀፍን ፡ የሚበልጥ ብድራቱን ፡ ትኩር ፡ ብሎ ፡ አይቷልና ሙሴ ፡ ጌታን ፡ አከበረው ፡ በሕይወት ፡ ጐዳና የማይታየውን ፡ በእምነት ፡ እያየ የዓለምን ፡ ክብር ፡ ሁሉ ፡ ስለ ፡ ጌታ ፡ ጣለ ጌታም ፡ አከበረው ፡ ልጁን ፡ አልተወውም ፀጋን ፡ አለበሰው ፡ ዓለም ፡ የማያየውን አዝ፦ በዓለም ፡ ከሚገኝ ፡ ብዙ ፡ ክብር ፡ ይልቅ ስለ ፡ ክርስቶስ ፡ መነቀፍን ፡ የሚበልጥ ብድራቱን ፡ ትኩር ፡ ብሎ ፡ አይቷልና ሙሴ ፡ ጌታን ፡ አከበረው ፡ በሕይወት ፡ ጐዳና እምነቴን ፡ በስራ ፡ እንድገልጠው የግለት ፡ መንፈስህን ፡ በሕይወቴ ፡ አብዛው እስከሞትም ፡ እንኳ ፡ ለስምህ ለመጋደል ፡ አብቃኝ ፡ እባክህ አዝ፦ በዓለም ፡ ከሚገኝ ፡ ብዙ ፡ ክብር ፡ ይልቅ ስለ ፡ ክርስቶስ ፡ መነቀፍን ፡ የሚበልጥ ብድራቱን ፡ ትኩር ፡ ብሎ ፡ አይቷልና ሙሴ ፡ ጌታን ፡ አከበረው ፡ በሕይወት ፡ ጐዳና