Loading
Singer
ገነት ፡ መኖሪያዬን ፡ ሰርተህ ፡ ውብ ፡ አድርገህ ምግቤን ፡ ያለ ፡ ድካም ፡ እንድበላ ፡ ብለህ ያስቀመጥክኝን ፡ ሰው ፡ ወሬ ፡ ሲደልለኝ እጦት ፡ ሲያራቁተኝ ፡ በቸልታ ፡ አትየኝ አዝ፦ ባስቀመጥከኝ ፡ ቦታ ፡ ፀንቼ ፡ እንድቆይ መጥተህ ፡ ስትጐበኘኝ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ እንዲልህ ፀጋህን ፡ አብዛልኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ ልቤ ፡ እየቸኮለ ፡ እግሬ ፡ ሮጥ ፡ እያለ ውርደትን ፡ ለማየት ፡ ዓይኔ ፡ እየከጀለ ድንበር ፡ እየጣሰ ፡ ከኃጢአት ፡ እየዋለ የማታ ፡ የማታም ፡ ሚዛኔ ፡ ቀለለ አዝ፦ ባስቀመጥከኝ ፡ ቦታ ፡ ፀንቼ ፡ እንድቆይ መጥተህ ፡ ስትጐበኘኝ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ እንዲልህ ፀጋህን ፡ አብዛልኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ የጭንጫ ፡ ቡቃያ ፡ ፈጥኖ ፡ የበቀለ ፀሐይ ፡ ስትወጣ ፡ ነዶ ፡ ተቃጠለ አንተን ፡ ሆኜ : እኔ ፡ ፍሬን ፡ እንዳፈራ አንስተህ ፡ አትጣለኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አደራ አዝ፦ ባስቀመጥከኝ ፡ ቦታ ፡ ፀንቼ ፡ እንድቆይ መጥተህ ፡ ስትጐበኘኝ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ እንዲልህ ፀጋህን ፡ አብዛልኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ ቸኮል ፡ ያለ ፡ ሳዖል ፡ በዓይኖችህ ፡ ተንቆ ብላቴናው ፡ ዳዊት ፡ ተቀብቷል ፡ ልቆ ዓይኔን ፡ ግለጥና ፡ ስፍራዬ ፡ ልወቀው አሳድገኝ ፡ እንጂ ፡ ዕድሜዬን ፡ አትቁረጠው አዝ፦ ባስቀመጥከኝ ፡ ቦታ ፡ ፀንቼ ፡ እንድቆይ መጥተህ ፡ ስትጐበኘኝ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ እንዲልህ ፀጋህን ፡ አብዛልኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ