Loading
ሠማያቶች ፡ ይስሙ ፣ ይስሙ ፡ ምድር ፡ ታስተጋባ የምቀኘውን ፡ ቅኔ ፡ ያለኝን ፡ ምሥጋና የከንፈሬን ፡ ፍሬ ፣ ፍሬ ፡ በፊቱ ፡ ላፍስሰው ትናንት ፡ እንዳዜምኩት ፡ ደስታዬ ፡ በአንተው ፡ ነው በአንተ ፡ የታሰበ ፡ የተረዳ ፡ ሰው ጌታ ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ ማነው (፪x) እንደ ፡ እኔ ፡ ማነው ፡ ክብር ፡ ያየው እንደ ፡ እኔ ፡ ማነው ፡ ወግ ፡ ያየው እንደ ፡ እኔ ፡ ማነው ፡ ደስ ፡ ያለው እንደ ፡ እኔ ፡ ማነው ፡ ክብር ፡ ያየው እንደ ፡ እኔስ ፡ ማነው ፡ ወግ ፡ ያየው (፪x) በሄድኩበት ፡ ሁሉ ፣ ሁሉ ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ አወራለሁ ስላደረክልኝ ፡ ድንቅ ፡ ቆሜ ፡ ዘምራለሁ ከአደረከው ፡ አንዳች ፣ አንዳች ፡ አልጐደለብኝም ምርጫዬ ፡ ነህ ፡ አንተስ ፡ እስከ ፡ ለዘለዓለም በአንተ ፡ የታሰበ ፡ የተረዳ ፡ ሰው ጌታ ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ ማነው (፪x) እንደ ፡ እኔ ፡ ማነው ፡ ክብር ፡ ያየው እንደ ፡ እኔስ ፡ ማነው ፡ ወግ ፡ ያየው (፮x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.