Loading
Singer
ማልጄ ፡ ደግሞ ፡ ስነሳ ፡ ስለውለታህ ፡ ላነሳሳ ሌቱም ፡ አልበቃ ፡ አልበቃ ፡ አለኝ ቀኑም ፡ እጥር ፡ እጥር ፡ አለብኝ የተደረገልኝ ፡ ራሴው ፡ ነው ፡ የማውቀው ዛሬ ፡ እዚህ ፡ መድረሴ ፡ ጌታዬ ፡ በአንተ ፡ ነው ሳስበው ፡ የትላንቱን ፡ (አሃሃ) አሰቃቂ ፡ መንገዱን ፡ (ኦሆሆ) በፀጋህ ፡ ደገፍከኝና ፡ (አሃሃ) ገረመኝ ፡ አለፍኩትና (፪x) በአንተ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፬x) እረካሁ ፡ ከእጅህ ፡ ጠጥቼ ፡ (አሃሃ) ወጣሁት ፡ ጉልበት ፡ አግኝቼ ፡ (አሃሃ) አልቀረሁ ፡ በምድረ ፡ በዳ ፡ (አሃሃ) አትወድም ፡ ሰው ፡ እንዲጐዳ ፡ (አሃሃ) (፪x) በአንተ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፬x) አንተ ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ ፡ የምታስበው ፡ መልካም ፡ ነዉ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ የምታስበው ፡ መልካም ፡ ነዉ ቆጥሬው ፡ ተናግሬው ፡ (አሃሃ) ከውስጤ ፡ የማይወጣው ፡ (አሃሃ) ጌትዬ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገው ፡ (አሃሃ) ከቁጥር ፡ ያለፈ ፡ ነው ፡ (አሃሃ) (፪x) በአንተ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፬x)