Loading
Singer
በመቁሰሌ ፡ እየተሳለቁ ፡ ሳዝን ፡ ከእኔ ፡ እየራቁ ፡ ጨከኑ እርዳታ ፡ እንዳልጠይቅ ፡ ርቀዉኝ ፡ ፈጥነው ፡ ከእኔ ፡ ተነጠቁ ፡ አደሙ ከቶ ፡ እኔ ፡ ግን ፡ አልተረሳሁም ፡ አምላኬ ፡ ከክብሩ ፡ ሆኖ ፡ አሰበኝ ልቡ ፡ ራርቶልኝ ፡ በፍቅሩ ፡ ፈዋሽ ፡ እጆቹን ፡ ዘርግቶ ፡ ታደገኝ አዝ:- በአንተ ፡ አምላኬ ፡ ብዙ ፡ አልፌያለሁ ክንድህን ፡ ተማምኜ ፡ ተደግፌሃለሁ በአንተ ፡ ጌታ ፡ ብዙ ፡ አልፌያለሁ ክንድህን ፡ ተማምኜ ፡ ተደግፌሃለሁ የወጣት ፡ ጉልበቴን ፡ አፍስሼ ፡ ሃሳብ ፡ ዘወትር ፡ ተንተርሼ ፡ ዘመኔን የሰበሰብኩት ፡ ተበተነ ፡ የተማመንኩት ፡ ተነነ ፡ ዞር ፡ ስል ሰላም ፡ ፈልጌ ፡ ምድርም ፡ ሽቶኝ ፡ ቆይቼ ፡ የእግዚአብሄርን ፡ ደጅ ፡ ጠናሁት የጭንቀት ፡ ጩኽቴ ፡ ተሰምቶ ፡ አምላኬ ፡ ዘምበል ፡ ሲል ፡ አየሁት አዝ:- በአንተ ፡ አምላኬ ፡ ብዙ ፡ አልፌያለሁ ክንድህን ፡ ተማምኜ ፡ ተደግፌሃለሁ በአንተ ፡ ኢየሱስ ፡ ብዙ ፡ አልፌያለሁ ክንድህን ፡ ተማምኜ ፡ ተደግፌሃለሁ ባጣ ፡ ባጣ ፡ ሁሉ ፡ ባይረባኝ ፡ ከሁሉ ፡ የምትበልጠውን ፡ ጌታዬን ስላገኘሁ ፡ ክብር ፡ ይሰማኛል ፡ ጓደኝነጥትህ ፡ ያረካታል ፡ ሕይወቴን ዘመኔን ፡ ለእጅህ ፡ እሰጣለሁ ፡ ሕይወቴን ፡ በእግርህ ፡ ስር ፡ ጌታ ፡ አኖራለሁ አንተ ፡ አደራ ፡ የማትበላ ፡ ታማኝ ፡ ወዳጅ ፡ መሆንህን ፡ ሰምቻለሁ አዝ:- በአንተ ፡ አምላኬ ፡ ብዙ ፡ አልፌያለሁ ክንድህን ፡ ተማምኜ ፡ ተደግፌሃለሁ በአንተ ፡ ጌታ ፡ ብዙ ፡ አልፌያለሁ ክንድህን ፡ ተማምኜ ፡ ተደግፌሃለሁ