Loading
Singer
አዝ፦ ባነበብነው ፡ በሰማነው ፡ ብቻ ፡ መች ፡ ሆነና ፡ የተከተልንህ ሕያው ፡ ምስክር ፡ ነን ፡ እኛም ፡ አየንህ እነዚህን ፡ የሚያህሉ ፡ ምስክሮች ፡ አሉ ፡ በዙሪያችን እኛም ፡ ደግሞ ፡ ሃያል ፡ ክንድህ ፡ ድንቅ ፡ አድርጐ ፡ አይተናል ፡ በዓይናችን እግዚአብሔር ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ ከምንልህ ፡ በላይ ሥምህ ፡ ብሩክ ፡ ይሁን ፡ በምድር ፡ በሰማይ (፪x) አዝ፦ ባነበብነው ፡ በሰማነው ፡ ብቻ ፡ መች ፡ ሆነና ፡ የተከተልንህ ሕያው ፡ ምስክር ፡ ነን ፡ እኛም ፡ አየንህ በነፍሳችን ፡ እንዳንዝል ፡ እንዳንደክም ፡ ደግፎ ፡ የሚያቆመን ለአንድ ፡ አፍታም ፡ የማንረሳው ፡ የማንጥለው ፡ ድንቅ ፡ ታሪክ ፡ አለን የነገው ፡ ደመና ፡ የሚያጨልመው ፡ ነገር አይከለክለንም ፡ አንተን ፡ ከማመስገን (፪x) አዝ፦ ባነበብነው ፡ በሰማነው ፡ ብቻ ፡ መች ፡ ሆነና ፡ የተከተልንህ ሕያው ፡ ምስክር ፡ ነን ፡ እኛም ፡ አየንህ አይተንሃል ፣ ሰምተንሃል ፣ ዳሰንሃል ፣ እንመሰክራለን እንደ ፡ ጠላታችን ፡ ምኞት ፡ አልጠፋንም ፡ ዛሬም ፡ በሕይወት ፡ አለን በሆነልን ፡ ነገር ፡ ብዙ ፡ ተደንቀናል የአባታችን ፡ መንግሥት ፡ ገና ፡ ይጠብቀናል (፪x) አዝ፦ ባነበብነው ፡ በሰማነው ፡ ብቻ ፡ መች ፡ ሆነና ፡ የተከተልንህ ሕያው ፡ ምስክር ፡ ነን ፡ እኛም ፡ አየንህ ጻድቅ ፡ ፈራጅ ፡ እውነተኛ ፣ ፊትን ፡ አይተህ ፡ ፈጽሞ ፡ አታደላ ፀሐይ ፡ ለጠለቀችበት ፡ ለጨነቀው ፣ ትሰጣለህ ፡ መላ ጊዜ ፡ ደረሰና ፡ ሁሉም ፡ ልኩ ፡ ታውቋል የሳቀ ፡ ሲያለቅስ ፣ ያለቀሰም ፡ ስቋል (፪x) አዝ፦ ባነበብነው ፡ በሰማነው ፡ ብቻ ፡ መች ፡ ሆነና ፡ የተከተልንህ ሕያው ፡ ምስክር ፡ ነን ፡ እኛም ፡ አየንህ