Loading
Singer
በአምላኬ ፡ ደስ ፡ አለኝ በፍቅሩ ፡ ረካሁኝ (፪x) ሕዝብህን ፡ ለማዳን ፡ ፈጥነህ ፡ ትነሣለህ የተቀባውንም ፡ ትታደገዋለህ እኔስ ፡ መጠጋቴ ፡ አንተኑ ፡ ላምን ፡ ነው መፎከሪያዬ ፡ ነህ ፡ የሚነካኝ ፡ ማነው (፫x) አዝ፦ ማነው ፡ ጌታ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ማነው ፡ እንዳንተ ፡ የሚወደው ማነው ፡ ኧረ ፡ እርሱ ፡ ማነው (፪x) አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ የሚሆን አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ የሚደርስ አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ የሚወድ አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ የሚራራ (፪x) አንተ ፡ የሠራኸው ፡ ለእኔ ፡ ተቆጠረ ይኸ ፡ ደግሞ ፡ ሳያንስ ፡ ስሜ ፡ ተቀየረ ልሳቅ ፡ እንጂ ፡ በደንብ ፡ በከሳሼ ፡ ላይ መርገም ፡ ተሰበረ ፡ ኢየሱስን ፡ ሳይ መርገም ፡ ተሰበረ ፡ መድኃኒቱን ፡ ሳይ መርገም ፡ ተሰበረ ፡ ኢየሱስን ፡ ሳይ አዝ፦ ማነው ፡ ጌታ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ማነው ፡ እንዳንተ ፡ የሚወደው ማነው ፡ ኧረ ፡ እርሱ ፡ ማነው (፪x) አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ የሚሆን አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ የሚደርስ አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ የሚወድ አቤቱ ፡ እንዳንተ ፡ የሚራራ (፪x) የጠላቴን ፡ ራስ ፡ አስረግጠኸኛል ድልን ፡ እያበዛህ ፡ አስደንቀኸኛል ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ ፡ የእኔ ፡ እንደሆንክ ፡ ሳስብ ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ይወቅ ፡ አምላኬ ፡ መሆንህን (፫x) ማነው ፡ ጌታ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው ማነው ፡ እንዳንተ ፡ የሚወደው ማነው ፡ ኧረ ፡ እርሱ ፡ ማነው (፪x) በአምላኬ ፡ ደስ ፡ አለኝ በፍቅሩ ፡ ረካሁኝ (፪x)