Loading
Singer
Updated 10/12/2026
በአምላክ ፡ አምሳል ፡ ተፈጥሬ ፡ በጐ ፡ ለማድረግ ፡ በፊቱ ስኖር ፡ ሳለሁ ፡ ኃጥያቴ ፡ አድርጐኝ ፡ ነበር ፡ ከንቱ ክቡር ፡ ሆኜ ፡ ሳለሁ ፡ አምላኬን ፡ ረስቼ እንደሚጠፉ ፡ እንስሶች ፡ መሰልኩ እኔ ፡ ሳልፈልገው ፡ ጌታ ፡ ሊፈልገኝ ፡ ከላይ ፡ መጥቶ ከእርኩሰት ፡ ውስጥ ፡ ነጥቆ ፡ አወጣኝ ፡ በዓለም ፡ ላይ ፡ ተንከራቶ ሸክሜን ፡ ወሰደልኝ ፡ በሥጋዬ ፡ ሞተልኝ የማይቆጠረውን ፡ በደሌን ፡ ፋቀልኝ መድኃኒቴ ፡ ነው ፡ ኢየሱሴ ፡ ጌታዬና ፡ አምላኬ ስለ ፡ መልካሙ ፡ ውለታው ፡ ላመስግነው ፡ ተንበርክኬ ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ማዳኑ ፡ ግሩም ፡ ነው ለአምላካዊ ፡ ፍቅሩ ፡ መጨረሻ ፡ የለው በሞት ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ እያለሁ ፡ በድቅድቅ ፡ ጨለማ ኢየሱስ ፡ ብርሃኔ ፡ መጥቶ ፡ አዳነኝ ፡ መሀሪ ፡ ነውና ለፍርድ ፡ የተመደብኩ ፡ ለሲዖል ፡ የታጨሁ የቁጣ ፡ ልጅ ፡ ስሆን ፡ ከፍጥረቴ ቅጣቴን ፡ ውስዶ ፡ ያ ፡ ረድኤቴ (፪x)