Loading
Singer
እወድሃለሁ ፡ ጌታ ፡ አድነኸኛል አመልክሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ቤዛ ፡ ሆነኸኛል አመሰግናለሁ ፡ ጌታ ፡ ታድገኸኛል አከብርሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ልጅ ፡ አድርገኸኛል ላመስግንህ ፡ ጠዋትና ፡ ማታ ከዚህ ፡ በላይ ፡ ይገባሃል ፡ ጌታ ላመስግንህ ፡ ጠዋትና ፡ ማታ ይሄ ፡ ብቻ ፡ አይበቃህም ፡ ጌታ ከሞት ፡ መንደር ፡ በምህረትህ ፡ በቸርነትህ ፡ አውጥተህ ጨለማውን ፡ አስወግደህ ፡ ለዚህ ፡ ክብር ፡ ያበቃኸኝ ሳትሰለች ፡ እያባበልክ ፡ ኃጢአት ፡ በደሌን ፡ ታግሰህ ሰው ፡ አረግከኝ ፡ አተረፍከኝ ፡ ነፍሴን ፡ ከጥፋት ፡ መልሰህ አዝ፦ ባለውለታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ባለውለታዬ ባለውለታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ዋሴ ፡ ጠበቃዬ (፪x) ያለ ፡ እረኛ ፡ ስቅበዘበዝ ፡ በዓለም ፡ ወጥመድ ፡ ተይዤ ፈጣሪዬን ፡ ስበድል ፡ ሳሳዝን ፡ በክፉ ፡ ደንዝዤ እራራህልኝ ፡ ደረስክልኝ ፡ ጸያፍ ፡ ታሪኬን ፡ ቀየርከው ልጅ ፡ ተባልኩኝ ፡ ክብር ፡ አገኘሁ ፡ ስሜን ፡ በደም ፡ ቀለም ፡ ጻፍከው አዝ፦ ባለውለታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ባለውለታዬ ባለውለታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ዋሴ ፡ ጠበቃዬ (፪x)