Loading
የደህንነቴ ፡ መደምደሚያ የክብር ፡ ስሜ ፡ ነህ ፡ መጠሪያ ማዕረጌ ፡ ሆነህ ፡ በሞትህ እኔም ፡ ተባልኩኝ ፡ ልጅህ (፪x) የሞትህ ፡ ፍሬ ፡ የድካምህ በጣር ፡ የወለድከኝ ፡ ልጅህ በመከራ ፡ አልፈህ ፡ ያገኘኀኝ የዕንባህ ፡ ልጅህ ፡ ነኝ (፪x) አዝ:- እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ ፡ እኔ የፍቅርህ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ውለታህ ፡ ያለብኝ እንዴት ፡ እንዴት ፡ ብዬ ፡ ነው መክፈል ፡ የምችለው ፡ የፍቅርህን ፡ ሸክም መቼም ፡ የማልመልሰው ልክፈል ፡ እንኳን ፡ ብዬ ፡ ብጀምር ፡ ማለዳ ፍቅርህን ፡ እንዲያው ፡ ሰጥተኀኛል ታዲያ ፡ አይደለሁም ፡ ወይ ፡ የፍቅርህ ፡ ባለ ፡ ዕዳ መራመድ ፡ አይችሉም ፡ እግሮቼ ኢየሱስ ፡ በፍቅርህ ፡ ተይዤ እንዳልሄድ ፡ ከቶ ፡ ወደሌላ አርገኝ ፡ የፍቅርህ ፡ እስረኛ አርገኝ ፡ የፍቅርህ ፡ እስረኛ እንዳልሄድ ፡ ከቶ ፡ ወደሌላ ኢየሱስ ፡ በፍቅርህ ፡ ተይዤ መራመድ ፡ አይችሉም ፡ እግሮቼ አዝ:- ንግሥና ፡ መጣ ፡ በደምህ እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ ክነቱም ፡ መጣ ፡ በሞት ኧረ ፡ እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ ደህንነት ሆነ ፡ በጸጋ እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ ልጅ ፡ መባል ፡ ቢሆን ፡ በስራህ እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ እኔማ ፡ የፍቅርህ ፡ ባለ ፡ ዕዳ የምህረትህ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ መራመድ ፡ አልችልም ፡ እግሬ ተይዣለሁ ፡ እኔ ነፍሱን ፡ ለወዳጁ ፡ ሚሰዋ ይገኝ ፡ ይሆናል ፡ በመከራ ኢየሱስ ፡ የአንተ ፡ ግን ፡ ሚገርመው ለጠላትህ ፡ የሞትከው (፪x) እድሜ ፡ ዘመኔን ፡ የሚገዛ ልቤን ፡ የያዘ ፡ ውለታህ የፍቅር ፡ ዕዳ ፡ አኖርክብኝ ሳልወድህ ፡ ወደድከኝ (፪x) አዝ:- መልክህና ፡ ውበትህ ፡ ጠፋ እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ በሰው ፡ ተንቀህ ፡ ተጠላህ ኧረ ፡ እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ ተፈወስኩኝ ፡ አንተ ፡ ቆስለህ እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ ደዌ ፡ ህመሜን ፡ ወሰድህ ኧረ ፡ እኔ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነኝ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.