Loading
Singer
አዝ፦ ጌታ ፡ አንተን ፡ ስለምን ጌታ ፡ አንተን ፡ ስጠራ ጌታ ፡ ደጁን ፡ ሳንኳኳ ኦ ፡ ሄይ (፪x) አይቼ ፡ የማላውቀው ፡ ጆሮዬም ፡ ያልሰማው አፈለቅህ ፡ ለእኔ ፡ ከአለቱ ፡ ውሃ ባሕር ፡ ከፍለሃል ፡ ማዕበሉን ፡ ገስጸህ እኔን ፡ አሻገርክ ፡ በደረቅ ፡ መሬት ሰማያዊ ፡ ነው ፡ የተሰጠኝም ፡ ዜግነት እርስቱ ፡ አድርጎ ፡ የሚገዛበት ታድገህኛል ፡ የበጉን ፡ ደም ፡ ለእኔ ፡ አፍሰህ ፍርዴን ፡ አስቀረኸው ፡ መስዋእት ፡ ሆነህ ትጥቅና ፡ ምግቤ ፡ ተለይቶ ፡ በግብጽ ፡ ማታ አረማመዴ ፡ ታዟል ፡ ከጌታ አዝ፦ ጌታ ፡ አንተን ፡ ስለምን ጌታ ፡ አንተን ፡ ስጠራ ጌታ ፡ ደጁን ፡ ሳንኯኯ ኦ ፡ ሄይ (፪x) ገበሬው ፡ አብ ፡ ነው ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ የአምላኬ ፡ እርሻ የማይጠፋው ፡ ዘር ፡ የማፈራበት ልብሴ ፡ አያረጅም ፡ ጫማዬም ፡ ከቶ ፡ አያልቅም በትንሳኤው ፡ ሃይል ፡ ሕይወቴ ፡ ጸንቷል አዝ፦ ጌታ ፡ አንተን ፡ ስለምን ጌታ ፡ አንተን ፡ ስጠራ ጌታ ፡ ደጁን ፡ ሳንኯኯ ኦ ፡ ሄይ (፪x)