Loading
Singer
አዝ፦ ባዶ ፡ ሸለቆን ፡ ይሞላል ምድረ ፡ በዳውን ፡ ያለመልማል ነፋስ ፡ ዝናብ ፡ ባይኖርም ተዓምር ፡ መስራቱ ፡ ፈፅሞ ፡ አይቀርም (፪x) ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይችላል (፬x) የቤት ፡ የጓዳው ፡ መብል ፡ ተሟጦባቸው ፡ ድረስ ፡ ና ፡ ላሉት በእንባ ፡ በጸሎታቸው ፡ እየጮሁ ፡ ለተማጸኑት መንገድ ፡ አለው ፡ መላ ፡ በመልሱ ፡ የሚያሳርፍበት የደረቀውን ፡ ኑሮ ፡ በቸርነቱ ፡ የሚያለመልምበት አዝ፦ ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይችላል (፬x) ባዶ ፡ ሸለቆን ፡ ይሞላል ምድረ ፡ በዳውን ፡ ያለመልማል ነፋስ ፡ ዝናብ ፡ ባይኖርም ተዓምር ፡ መስራቱ ፡ ፈፅሞ ፡ አይቀርም ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይችላል (፬x) የቀጠረለትን ፡ ቀን ፡ ምስኪኑን ፡ የሚባርክበት ይጠብቃል ፡ አውቀን ፡ ምን ፡ እንደተዘጋጀለት ያያል ፡ እጁ ፡ ሲገባ ፡ ሲያቆምለት ፡ ያን ፡ የደም ፡ እንባ የሱም ፡ ደሳሳ ፡ ጐጆ ፡ ሰው ፡ በማይንቅ ፡ አምላክ ፡ ታስባ አዝ፦ ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይችላል (፬x) ባዶ ፡ ሸለቆን ፡ ይሞላል ምድረ ፡ በዳውን ፡ ያለመልማል ነፋስ ፡ ዝናብ ፡ ባይኖርም ተዓምር ፡ መስራቱ ፡ ፈፅሞ ፡ አይቀርም ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይችላል (፬x) ድንጉጥ ፡ ልበ ፡ ፈሪዎች ፡ ለሰጉ ፡ ለተጠራጣሪዎች ስለ ፡ ነገ ፡ ተጨንቀው ፡ የትላንቱን ፡ ተዓምር ፡ ለረሱ ፡ ሰዎች መልዕክት ፡ አለው ፡ ዛሬም ፡ እኔ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ አልተለወጥኩም ይመስክሩ ፡ ልጆቼ ፡ ተስፋ ፡ ያረጉኝን ፡ አላሳፈርኩም አዝ፦ ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይችላል (፬x) ባዶ ፡ ሸለቆን ፡ ይሞላል ምድረ ፡ በዳውን ፡ ያለመልማል ነፋስ ፡ ዝናብ ፡ ባይኖርም ተዓምር ፡ መስራቱ ፡ ፈፅሞ ፡ አይቀርም ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይችላል (፬x) ቀንበር ፡ ለከበዳቸው ፡ የዚህ ፡ ዓለም ፡ ኑሮ ፡ ለመረራቸው ቀኙን ፡ ግራውን ፡ ቢሉ ፡ ቢንከራተቱ ፡ ላልሞላላቸው እንጀራ ፡ ላጡ ፡ እንጀራ ፡ ባርኮ ፡ ሰጥቶ ፡ ያቀርባችኋል ብዙ ፡ ረሃባችሁን ፡ በብዙ ፡ ጥጋብ ፡ ይለውጥላችኋል አዝ፦ ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይችላል (፬x) ባዶ ፡ ሸለቆን ፡ ይሞላል ምድረ ፡ በዳውን ፡ ያለመልማል ነፋስ ፡ ዝናብ ፡ ባይኖርም ተዓምር ፡ መስራቱ ፡ ፈፅሞ ፡ አይቀርም ይችላል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይችላል (፬x)