Loading
Singer
አዝ፦ መውጣትህ ፡ መግባትህ ፡ በእግዚአብሔር ፡ እጅ ፡ ነው ታዲያ ፡ የምትፈራው ፡ ምትሰጋው ፡ ምንድነው የሚያሰጋህ ፡ ታዲያ ፡ የቱ ፡ ነው (፪x) በሁሉም ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ የበላይ ፡ ነው (፪x) ዙሪያህ ፡ የከበበህ ፡ ሁኔታ ፡ የማይሆን ፡ ቢመስልህ የምታየው ፡ ሁሉ ፡ ቢዘጋ ፡ ግራ ፡ ቢገባህም የምትፈራው ፡ ነገር ፡ ላይወርስህ አይዞህ ፡ ኢየሱስ ፡ አለልህ አዝ፦ መውጣትህ ፡ መግባትህ ፡ በእግዚአብሔር ፡ እጅ ፡ ነው ታዲያ ፡ የምትፈራው ፡ ምትሰጋው ፡ ምንድነው የሚያሰጋህ ፡ ታዲያ ፡ የቱ ፡ ነው (፪x) በሁሉም ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ የበላይ ፡ ነው (፪x) ሰበሰብኩኝ ፡ ስትል ፡ ያያዝከው ፡ከእጅህ ፡ ቢበተንም ተስፋ ፡ ያረከው ፡ ሁሉ ፡ እርቆ ፡ አልያዝ ፡ ቢልህም በእግዚአብሔር ፡ ሀሳብ ፡ ላይ ፡ ኑር ፡ እንጂ አይዞህ ፡ አለህ ፡ ወዳጅ አዝ፦ መውጣትህ ፡ መግባትህ ፡ በእግዚአብሔር ፡ እጅ ፡ ነው ታዲያ ፡ የምትፈራው ፡ ምትሰጋው ፡ ምንድነው የሚያሰጋህ ፡ ታዲያ ፡ የቱ ፡ ነው (፪x) በሁሉም ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ የበላይ ፡ ነው (፪x) አልጥልህም ፡ ብሎ ፡ የጠራህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ታማኝ ፡ ነው ላንተ ፡ ባይመስልህም ፡ አላማው ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው ሳትፈራ ፡ ጥቂት ፡ ታገሰው ጽና ፡ ማጉረምረሙን ፡ ተወው አዝ፦ መውጣትህ ፡ መግባትህ ፡ በእግዚአብሔር ፡ እጅ ፡ ነው ታዲያ ፡ የምትፈራው ፡ ምትሰጋው ፡ ምንድነው የሚያሰጋህ ፡ ታዲያ ፡ የቱ ፡ ነው (፪x) በሁሉም ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ የበላይ ፡ ነው (፪x)