Loading
Singer
ነገን ፡ ነገን ፡ ስታይ ፡ ቢጨልምብህ/ከጨልምብህ በተስፋ ፡ ተራመድ ፡ እራዕይ ፡ ይኑርህ/አለህ (፪x) አይዞህ (፫x) ሥራ ፡ ብታጣ ፡ ገንዘብ ፡ ቢጠፋ ቢጨልምብህ ፡ አይዞህ ሚረዳህ ፡ አጥተህ ፡ ብቻህን ፡ ብትሆን ተስፋ ፡ ባይኖርህ ፡ አይዞህ (፪x) አስሩን ፡ ስታስብ ፡ ሚሰማህ ፡ እንዳነስህ ከሁሉ ፡ የበታች ፡ የሆንክ ፡ የመሰለህ አይዞህ (፫x) ልዩ ፡ የሆነ ፡ ችሎታ ፡ አለህ ተነስ ፡ ታገል ፡ አይዞህ ከማንም ፡ አታንስ ፡ ይኸው ፡ ራስህም ብቃት ፡ እኮ ፡ አለህ ፡ አይዞህ መስራት ፡ ማችልበት ፡ ምንም ፡ ምክኒያት ፡ የለ ጠንክረህ ፡ ብትሰራ ፡ ብዙ ፡ ታጭዳለህ አይዞህ (፫x) የረፈደብህ ፡ እየመሰልህ ትተክዛለህ ፡ አይዞህ በዚህ ፡ ጉብዝናህ ፡ በሙሉ ፡ ኃይልህ መራመድ ፡ ጀምር ፡ አይዞህ አንድ ፡ ቀን ፡ ያልፋል (፫x) የወደደ ፡ ያከበረ ፡ ያፈቀረ አምላክ ፡ አለህ ፡ አለህ የወደደ ፡ ያፈቀረ ፡ ያከበረ አምላክ ፡ አለህ ፡ አለህ