Loading
Singer
አዝ፦ ጌታ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ እውነተኛ ፡ ደስታ በከፍታ ፡ በዝቅታ ፡ አይወስንህ ፡ ሁኔታ አይወስንህ ፡ ሁኔታ (፪x) ከሠማይ ፡ በታች ፡ ፍጥረት ፡ የሚያገኘው ደስታው ፡ የማይጸና ፡ የከንቱ ፡ ከንቱ ፡ ነው ታዲያ ፡ ምብዛቱ ፡ ጥቅሙ ፡ ምንድን ፡ ነው ምኞቱ ፡ መሻቱ ፡ ንፋስ ፡ መከተሉ አዝ፦ ጌታ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ እውነተኛ ፡ ደስታ በከፍታ ፡ በዝቅታ ፡ አይወስንህ ፡ ሁኔታ አይወስንህ ፡ ሁኔታ (፪x) የዚች ፡ ዓለም ፡ ውብት ፡ መቼ ፡ ደስታ ፡ ይሰጣል ትናንት ፡ የነበረ ፡ ድንገት ፡ ከእጅ ፡ ያመልጣል ቋሚ ፡ ነገር ፡ የለም ፡ ለሁሉም ፡ ጊዜ ፡ አለው የሚጸና ፡ ደስታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው አዝ፦ ጌታ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ እውነተኛ ፡ ደስታ በከፍታ ፡ በዝቅታ ፡ አይወስንህ ፡ ሁኔታ አይወስንህ ፡ ሁኔታ (፪x) መብዛትን ፡ መጉደልን ፡ ሁሉ ፡ ተምሬያለሁ ኃይልን ፡ በሚሰጠኝ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ ነገር ፡ ተለዋዋጭ ፡ መሆኑን ፡ አየሁኝ የሚጸና ፡ ደስታ ፡ ጌታን ፡ አገኘሁኝ ደስታዬ ፡ አንተ ፡ ብቻ ሰላሜ ፡ አንተ ፡ ብቻ እረፍቴ ፡ አንተ ፡ ብቻ ሃብቴ ፡ አንተ ፡ ብቻ (፪x) አዝ፦ ጌታ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ እውነተኛ ፡ ደስታ በከፍታ ፡ በዝቅታ ፡ አይወስንህ ፡ ሁኔታ አይወስንህ ፡ ሁኔታ (፪x)