Loading
Singer
Updated 4d ago
እኔስ ፡ አልረሳሁም ፡ ያደረክልኝን ከጨለማ ፡ አውጥተህ ፡ ቀን ፡ ያወጣህልኝ (፪x) ምስኪኑን ፡ ከጉድፍ ፡ ከአመድ ፡ አንስተኸው ከታላላቆች ፡ ጋር ፡ ስፍራ ፡ እንደሰጠኸኝ (፪x) አይረሳኝም ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ያረክልኝ ፡ ብዙ ፡ ውለታ አይረሳኝም ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ስለእኔ ፡ ተንገላታህ አይረሳኝም ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ያረክልኝ ፡ ብዙ ፡ ውለታ አይረሳኝም ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ የሆንክልኝ ፡ በጐልጐታ መቆም ፡ መቀመጤን ፡ በፊትህ ፡ አድርገህ ክፉ ፡ አንዳይነካኝ ፡ በዙሪያዬ ፡ ሆነህ (፪x) የአመጽ ፡ ፈሳሽ ፡ አልፎ ፡ ቀን ፡ ወጣልኝ ፡ ለእኔ ምክንያቱ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ ለመዳኔ (፪x) የመኖሬ ፡ ምክንያቱ ፡ አንተ ፡ ነህ (፪x) የመክበሬ ፡ ምክንያቱ ፡ አንተ ፡ ነህ (፪x) የመቆሜ ፡ ምክንያቱ ፡ አንተ ፡ ነህ (፬x) የተቆረጠና ፡ የአለቀውን ፡ ነገሬን ቀጥለህልኛል ፡ አይተህ ፡ መቸገሬን (፪x) ብቻህን ፡ ያለአጋዥ ፡ የረዳኸን ፡ ጌታ ዘምረ ፡ ያሰኘኛል ፡ በዝቶ ፡ የአንተ ፡ ውለታ (፪x) የመኖሬ ፡ ምክንያቱ ፡ አንተ ፡ ነህ (፪x) የመክበሬ ፡ ምክንያቱ ፡ አንተ ፡ ነህ (፪x) የመቆሜ ፡ ምክንያቱ ፡ አንተ ፡ ነህ (፬x)