Loading
መልካም ፡ ዘመን ፡ ወይም ፡ ክፉ አያወጡኝ ፡ ከእቅፉ ዓይን ፡ ያላየው ፡ ጆሮ ፡ ያልሰማው አለው ፡ ለእኔ ፡ ያዘጋጀው አጋጣሚውን ፡ ልቤ ፡ አይቶ አይሸፍትም ፡ ከሱ ፡ ወጥቶ ግራ ፡ ገብቶኝ ፡ ዝዬ ፡ አልቅሼ ጌታ ፡ አይደል ፡ ዎይ ፡ አስታዋሼ አዝ፦ አይረሳም ፡ ሰው ፡ አይረሳም (፬x) እስኪ ፡ ልናገር ፡ ካልኩት ፡ በላይ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ነገር በዓለም ፡ ያልታየ ፡ በሰው ፡ የሌለ ፡ የሰማይ ፡ ፍቅር እስኪ ፡ ልናገር ፡ ካልኩት ፡ በላይ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ስራ በዓለም ፡ ያልታየ ፡ በሰው ፡ የሌለ ፡ አያልቅ ፡ ቢወራ እጄን ፡ ይዞ ፡ እንዳልዎድቅ ሲራራልኝ ፡ ሲጠነቅቅ አቤት ፡ ሲያዝን ፡ አቤት ፡ ሲሳሳ የኔን ፡ ነገር ፡ ፍፁም ፡ አይረሳ (፪x) አዝ፦ አይረሳም ፡ ሰው ፡ አይረሳም (፬x) ስላለፈው ፡ ስጨነቅ ስለነገው ፡ ስታወክ መለስ ፡ ስል ፡ ወደ ፡ ልቤ ጌታ ፡ እኮ ፡ አለ ፡ አጠገቤ ምክንያቱ ፡ ነው ፡ ለመኖሬ ለሱኮ ፡ ነው ፡ መፈጠሬ ከበደኝ ፡ አይል ፡ ሲሸከመኝ ከኔ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ መቼ ፡ ረሳኝ እስኪ ፡ ልናገር ፡ ካልኩት ፡ በላይ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ነገር በዓለም ፡ ያልታየ ፡ በሰው ፡ የሌለ ፡ የሰማይ ፡ ፍቅር እስኪ ፡ ልናገር ፡ ካልኩት ፡ በላይ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ስራ በዓለም ፡ ያልታየ ፡ በሰው ፡ የሌለ ፡ አያልቅ ፡ ቢወራ እጄን ፡ ይዞ ፡ እንዳልዎድቅ ሲራራልኝ ፡ ሲጠነቅቅ አቤት ፡ ሲያዝን ፡ አቤት ፡ ሲሳሳ የእኔን ፡ ነገር ፡ ፍፁም ፡ አይረሳ (፪x) አዝ፦ አይረሳም ፡ ሰው ፡ አይረሳም (፬x) እናት ፡ ልጇን ፡ ብትረሳ ዓይኗን ፡ ከእርሱ ፡ ብታነሳ ብትሸከም ፡ አልፈጠረች እንደሌላው ፡ ሰው ፡ እኮ ፡ ነች በእስትንፋሱ ፡ የሰራኝ ፡ ግን ሊያጣኝ ፡ አይወድ ፡ ሌትና ፡ ቀን ዋጋ ፡ ከፍሎ ፡ ዋጋ ፡ ሰጠኝ መች ፡ ሊረሳ ፡ መች ፡ ሊተወኝ ለካ ፡ ሸክሙ ፡ የሚከብደው ሰው ፡ ለብቻው ፡ ሲዪዘው ፡ ነው ሲደርስልኝ ፡ በድካሜ እርፍ ፡ አልኩኝ ፡ ከህመሜ ቀን ፡ ያነሳው ፡ ቀን ፡ ቢሽረው ጌታ ፡ ያሰበውን ፡ ሰው ፡ አይጥለው በንስር ፡ ክንፍ ፡ በከፍታ ያወጣኛል ፡ የእኔ ፡ ጌታ አዝ፦ አይረሳም ፡ ሰው ፡ አይረሳም (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.