Loading
Singer
አዝ፦ ጌታ ፡ ምስኪኖችን ፡ ይወዳል ጐስቋሎችን ፡ ይወዳል ሰው ፡ የጣለውን ፡ ያነሳል የተረሳውን ፡ ያስታውሳል ዓይኖቹ ፡ በምድር ፡ ሁሉ ፡ ያያሉ ለዓይነስውራን ፡ መሪ ፡ ነው ለአካለ ፡ ስንኩል ፡ ድጋፍ ፡ ነው ለረሃብተኞች ፡ መጋቢ ወላጅ ፡ አልባውን ፡ ሰብሳቢ ለደሃ ፡ አደጐች ፡ አባት ፡ ነው ለመበለቶች ፡ ዳኛ ፡ ነው ሃዘንተኛውን ፡ ያጽናናል ጌታ ፡ ለሁሉም ፡ ይሆናል ጌታ ፡ ሰርግ ፡ ቤት ፡ ይገኛል ውሃውን ፡ ወይን ፡ ጠጅ ፡ ያደርጋል በለቅሶም ፡ በሀዘን ፡ ቦታ ተገኝቶ ፡ ያጽናናል ፡ ጌታ ህመመተኛውን ፡ ደጋፊ አስታማሚ ፡ አልጋ ፡ አንጣፊ ሐኪም ፡ ነው ፡ በሽታን ፡ ያውቃል ፈዋሽ ፡ ነው ፡ ነጻ ፡ ያወጣል ካህን ፡ ነው ፡ ሕዝብን ፡ ይመራል ንጉሥ ፡ ነው ፡ ያስተዳድራል ወታደር ፡ ነው ፡ አገር ፡ ጠባቂ ከአውሬ ፡ ከአንበሳ ፡ ነጣቂ አገር ፡ ሲወረር ፡ በግፍ ሕዝብ ፡ እንደ ፡ ቅጠል ፡ ሲርግፍ ከምስኪኖች ፡ ጐን ፡ ይቆማል መርከቡን ፡ በባሕር ፡ ያሰጥማል ሃዘን ፡ ትጥቅህን ፡ አይፍታ ችግርክን ፡ ንገር ፡ ለጌታ አያልፍም ፡ ከንፈሩን ፡ መጥጦ ያነሳል ፡ እጅን ፡ ጨብጦ