Loading
Singer
አዝ፦ አየሁ ፡ እኔስ ፡ እኔስ ፡ አየሁ በዚህች ፡ እድሜ ፡ ስንቱን ፡ አየሁ በዙፋኑ ፡ ፀንቶ ፡ ያለው እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ ሁሌም ፡ ያው ፡ ነው (፪x) እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ ሁሌም ፡ ያው ፡ ነው (፮x) ትላንት ፡ ሲታይ ፡ ማይደፈር ፡ ሲባል ፡ ዛሬ ፡ አይን ፡ ላፈር አንቱ ፡ መባል ፡ ትላንት ፡ አንሶት ፡ ዛሬ ፡ አንተነት ፡ ሲበዛበት ሰው ፡ ወዶ ፡ የሾመውን ፡ ሰው ፡ ወዶ ፡ ይሸረዋል (፪x) ከእኛ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ ግን ፡ ማን ፡ ይስተካከላል ከዘለአለምም ፡ እስከ ፡ ዘለአለም (፪x) ነው ፡ መንግስቱ ፡ ጽኑ ፡ የሚመስለው ፡ የለም አዝ፦ ህያው ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ህያው ፡ ነው (፪x) ጌታ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x) አንድ ፡ ሺ ፡ ቀን ፡ እንደአንድ ፡ ቀን አንድ ፡ ቀንም ፡ አንደአንድ ፡ ሺ ሁሌ ፡ ጌታ ፡ በዘመናት ፈጣሪያቸው ፡ ለእለታት በጊዜ ፡ አይገደብ ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሐር ፡ ነው (፪x) አመቶቹ ፡ አያልቁ ፡ ጸንቶ ፡ የሚኖር ፡ ነው ያሳልፋል ፡ እንጂ ፡ እርሱ ፡ አንደው ፡ አያልፍም (፪x) ተላንትናም ፡ ዛሬም ፡ ያው ፡ ነው ፡ ለዘላለም አዝ፦ ህያው ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ህያው ፡ ነው (፪x) ጌታ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x) አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ እርሱ ፡ እኮ ፡ ነው ለዘላለም ፡ ህያው ፡ እርሱ ፡ ነው ላሞጋግሰው ፡ ይህን ፡ ጌታ በጭብጨባ ፡ በእልልታ ክብርና ፡ ሞገስም ፡ ባለጠግነትም ፡ ሊቀበል ፡ የሚገባው ከጌቶቹ ፡ ጌታ ፡ ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ማን ፡ ነው ግርማው ፡ የተለየ ፡ ባለ ፡ ብዙ ፡ ዝና (፪x) ያለ ፡ አጋር ፡ እረዳት ፡ ብቻዉን ፡ ገናና አዝ፦ ህያው ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ህያው ፡ ነው (፪x) ጌታ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x) ጌታ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x) ህያው ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ህያው ፡ ነው (፪x) ጌታ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)