Loading
Singer
አየሁ (፫x) ፡ አሻግሬ ፡ አየሁ አምነው ፡ የሞቱትን ፡ ልመስል ፡ ተመኘሁ አብርሃምን ፡ አየሁ ፡ የእግዚአብሔርን ፡ ወዳጅ ይስሐቅን ፡ ሊሰዋ ፡ ለሰይፍ ፡ የሚያዘጋጅ ቃሉን ፡ ያከበረ ፡ ያን ፡ ቁም ፡ ነገረኛ በሀሳቡም ፡ ቁርጠኛ ፡ የእምነትን ፡ አርበኛ ስውር ፡ ጣዖት ፡ የለውም ፡ ከአምላኩ ፡ የሚነጥል በቀውጢ ፡ ዘመናት ፡ እምነቱን ፡ የሚያስጥል ሐዋርያትን ፡ አየሁ ፡ የፅድቅን ፡ ሰልፈኞች የኃጢአትን ፡ ጠሮች ፡ የእምነትን ፡ ቀንድኞች በአንድነት ፡ ፀሎት ፡ ምድርን ፡ ነቀነቋት በድል ፡ ብርሃን ፡ ወንጌል ፡ ባንዴ ፡ አጥለቀለቋት ከጌቶቹ ፡ ጌታ ፡ ፈቃድ ፡ ነበራቸው ሥልጣናት ፡ አልቻሉም ፡ ከቶ:ሊያግቷቸው ሰማዕታትን ፡ አየሁ ፡ እነ ፡ እስጢፋኖስን ዓለም ፡ ሲጠላቸው ፡ አምነው ፡ ኢየሱስን የደም ፡ ጥማተኞች ፡ ፍዳ ፡ ሲያሳዯዋቸው ፊታቸው ፡ ሲያበራ ፡ ያም ፡ ሳይበግራቸው ለዓለም ፡ ሲያማልዱ ፡ ልክ ፡ እንደ ፡ ጌታቸው አቤት ፡ ሲያስቀና ፡ ያ ፡ አሟሟታቸው ኮብላዮችን ፡ አየሁ ፡ ከጨለማ ፡ ገብተው ሲዖልና ፡ ሰይጣን ፡ ጌታም ፡ የለም ፡ ብለው በሥሙ ፡ ዘብተው ፡ በደሙ ፡ ቀልደው የለም ፡ ካሉት ፡ ጋራ ፡ በሞት ፡ ተገናኝተው መንፈሴ ፡ አያቸው ፡ በአንድነት ፡ ሲንጫጩ በሙታን ፡ ዓለም ፡ ውስጥ ፡ በእሳት ፡ ሲወራጩ እንግዲህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እኔነቴን ፡ ግዛ ኪዳኔን ፡ አጥፌ ፡ ሞትን ፡ እንዳልገዛ ብርሃኑ ፡ ደብዝዞ ፡ ጭጋጉ ፡ ሲከበኝ አንተው ፡ እየመራህ ፡ ወደ ፡ ላይ ፡ አዝልቀኝ የተፃፈው ፡ ሁሉ ፡ ለትምህርት ፡ ሆኖልኝ በፅናት ፡ ታግዬ ፡ እንዳሸንፍ ፡ እርዳኝ የተጻፈው ፡ ሁሉ ፡ ለትምህርት ፡ ሆኖልኝ ገድሉን ፡ ተጋድዬ ፡ እንዳሸንፍ ፡ እርዳኝ