Loading
Singer
ገንኖ ፡ ገንኖ ፡ ስምህ ፡ መውጣቱ ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ስላንተ ፡ ማውራቱ ከፍታ ፡ ላይ ፡ አለመድረሱ ፡ ይሄ ፡ ሁሉ ፡ ማዕረጉ ልክ ፡ ነው ፡ አይበዛብህ ፡ እንዲያውም ፡ ስያንስብህ (፫x) ማን ፡ ብሎህ ፡ ከበርህ ፡ አንተ ፡ እራስህ ፡ ክቡር ማን ፡ ሾሞህ ፡ ነገስህ ፡ አንተ ፡ እራስህ ፡ ንግስ ማን ፡ ብሎህ ፡ ክቡር ፡ ሆንክ ፡ ማን ፡ ሾሞህ ፡ ነገሥህ (፪x) አንተ ፡ እራስህ ፡ ክቡር ፡ ነህ (፪x) አንተ ፡ እራስህ ፡ ንጉስ ፡ ነህ (፪x) እራስህ ፡ አንተ ፡ እራስህ ፡ ክቡር ፡ ነህ እራስህ ፡ አንተ ፡ እራስህ ፡ ንጉሥ ፡ ነህ ጌታዬ ፡ እኔ ፡ ከምልህ ፡ አንተ ፡ ያለህ ፡ ብዙ ፡ ነው ስለገረመኝ ፡ ብቻ ፡ እንዲህ ፡ ነህ ፡ እልሃለሁ (፪x) ምስጋናዬን ፡ እሰማለሁ ፡ በከንፈሬ የወጣው ፡ ግን ፡ የሞላው ፡ ነው ፡ ነው ፡ ከልቤ አምልኮዬን ፡ እሰማለሁ ፡ በከንፈሬ የወጣው ፡ ግን ፡ የሞላው ፡ ነው ፡ ከልቤ ከልቤ ፡ ነው ፡ ከልቤ ፡ አይደለም ፡ በከንፈሬ (፪x) ዝማሬዬን ፡ አሰማለሁ ፡ በከንፈሬ የወጣው ፡ ግን ፡ የሞላው ፡ ነው ፡ ከልቤ አድናቆቴን ፡ አሰማለሁ ፡ በከንፈሬ የወጣው ፡ ግን ፡ የሞላው ፡ ነው ፡ ከልቤ ከልቤ ፡ ነው ፡ ከልቤ ፡ አይደለም ፡ በከንፈሬ (፪x) ክበር ፡ ይላሉ ፡ ንገሥ ፡ ይላሉ በሰማይ ፡ ያሉ ፡ በምድር ፡ ያሉ ሲሉህ ፡ ሰምቼ ፡ ልልህ ፡ ቆምኩኝ እኔም ፡ የራሴ ፡ ምሥጋና ፡ አለኝ (፪x) አለኝ ፡ ምሥጋና ፡ አለኝ አለኝ ፡ ዝማሬ ፡ አለኝ አለኝ ፡ አምልኮ ፡ አለኝ አለኝ ፡ አድናቆት ፡ አለኝ (፪x)