Loading
የማይታየውንና ፡ የሚታየውን ፡ በሙሉ በአንተ ፡ ተፈጠረ ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ በሙሉ ፡ በሙሉ በአንተ ፡ ተፈጠረ ፡ ሁሉ ፡ በሙሉ ፡ በሙሉ ትርጉም ፡ አለው ፡ ሁሉም ፡ አስተውሎ ፡ ተመለከተው ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ ሆነ ፡ ያልሆነውስ ፡ አንዳች ፡ የቱ ፡ ነው (፪x) ተወሰደ ፡ ልቤ ፡ በእሱኛው ፡ በእሱኛው ሰው ፡ በሰራው ፡ ሳይሆን ፡ እግዚአብሔር ፡ በሰራው ተማረከ ፡ ልቤ ፡ በእሱኛው ፡ በእሱኛው በምድራዊው ፡ ሳይሆን ፡ በሠማያዊው ፡ ነው አይ ፡ ጥበብ ፡ ሆሆ አይ ፡ ጥበብ (፬x) አይሰራ ፡ አይ ፡ ጥበብ ፡ ረቂቅ ፡ ነው በእርግጥ ፡ የማመልከው ፡ አምላክ ፡ ዕውቅታም ፡ ነው (፪x) የኮረብታውና ፡ የወንዙ ፡ የወፎች ፡ ጫጫታ ጌታ ፡ በእጁ ፡ ብቻ ፡ ሳይሆን ፡ በቃሉ ፡ ብቻ ፡ ፈጠረ በእጁ ፡ ሳይነካ ፡ በቃሉ ፡ ብቻ ፡ ፈጠረ የውቂያኖስና ፡ የባሕር ፡ የጥልቀቱ ትልቅ ፡ ነው ፡ ያሰኛል ፡ የጌታ ፡ አቤት ፡ ዕውቀቱ (፪x) በሥራው ፡ በዕውቀቱ ፡ የተደነቀው ፈጣሪውን ፡ ጌታ ፡ እኔ ፡ አመልከዋለሁ የሁሉ ፡ የበላይ ፡ የበላይ ፡ የሆነው እኔ ፡ የማመልከው ፡ እግዚአብሔር ፡ ጌታ ፡ ነው አይ ፡ ጥበብ ፡ ሆሆ አይ ፡ ጥበብ (፬x) አይሰራ ፡ አይ ፡ ጥበብ ፡ ረቂቅ ፡ ነው በእርግጥ ፡ የማመልከው ፡ አምላክ ፡ ዕውቅታም ፡ ነው (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.