Loading
Singer
ለአሉባልታ ፡ ጊዜ ፡ የለኝ ፡ እኔ አውርቼ ፡ አልጨረስኩ ፡ ስለመዳኔ አልጣላ ፡ ሁሉም ፡ የመጣው ፡ ከአንተ ፡በኋላ በመቦጫጨቅ ፡ ባርኮት ፡ አይመጣ ለውኃ ጥማት ፡ ውኃ አይጠጣ እስኪ ፡ እንጨብጥ ፡ እርፍ ፡ ማረሻ ሥራ ፡ ነውና ፡ የአገር ፡ መነሻ ፡ አሀ ፡ አሀ አርሰን ፡ ሳንዘራ ፡ መስከረም ፡ ጠባ አገር ፡ በወሬ ፡ አትገነባ ነገም ፡ እንዳያልፍ ፡ እንደ ፡ ትላንቱ ጉልበት ፡ ማንቃቱ ከአየር ፡ ከውሃው ፡ ምንም ፡ አላጣን ስላልሰራን ፡ ነው ፡ ረሃብ ፡ የቀጣን የሞተው ፡ ሞቶ ፡ ያለነው ፡ አለን ታጥቀን ፡ ከወጣን ፡ ነገ ፡ እንደርሳለን ፡ አሀአሀ መስመር ፡ ጠብቆ ፡ ሮጦ ፡ ማሸነፍ ወይስ ፡ በተንኮል ፡ ወንድምን ፡ መጥለፍ የትኛው ፡ ይሆን ፡ የተፈቀደው እኔ ፡ ትቻለሁ ፡ ህሊና ፡ ይፍረድ እጣ ፡ የደረሰው ፡ ትላንት ፡ ተገፋ ዛሬስ ፡ ማን ፡ ይሆን ፡ ባለወረፋ እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ እየን ፡ ከሰማይ የፍቅር ፡ ዘይት ፡ አፍስስ ፡ በእኛ ፡ ላይ የወሬ ፡ ጠላት ፡ ሥራን ፡ አፍቃሪ በውኃ በየብስ ፡ በአየር ፡ በራሪ የትውልድ ፡ ኩራት ፡ መድሃኒተኛ አምላካችን ፡ ሆይ ፡ አምጣልን ፡ ለእኛ