Loading
Singer
ግራና ፡ ቀኜን ፡ ከፊት ፡ ከኋላ ሲጨልምብኝ ፡ ባጣ ፡ ማረፊያ ተስፋዬ ፡ ያልኩት ፡ በእጄ ፡ ይዤ ድንገት ፡ ሲከዳኝ ፡ ብቀር ፡ ተክዤ የተውከኝ ፡ ሲመስለኝ ፡ አምላኬ ፡ ከላይ ምድር ፡ ጐርብጣ ፡ ቢዘጋ ፡ ሰማይ አሃሃ ፡ አውቃለሁ አንተ ፡ ሁልጊዜ ፡ ትክክል ፡ እንደሆንክ አውቃለሁ ፡ ተናግረህ ፡ ማትፈጽም ፡ ቀላባይ ፡ እንዳልሆንክ አዝ፦ አውቃለሁ ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ሃሳብ ፡ እንዳለህ ፍቅር ፡ ነው ፡ አላማህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ውዴ ፍቅር ፡ ነው ፡ አላማህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ውዴ (፪x) ሀጥያቴ ፡ ሲጋለጥ ፡ ለአሉታ ፡ ወሬ በነበር ፡ ሆኖ ፡ ሳይቀር ፡ ነገሬ የሽንፈት ፡ ቃላት ፡ ከአፌ ፡ እንዲወጣ ሲወተውተኝ ፡ ምክንያት ፡ ቢያጣ ሙሾ ፡ ሲደረድር ፡ ይኸው ፡ ጠፋሁ ፡ ብዬ በገናዬን ፡ ስጥል ፡ ሊስቅ ፡ ባላንጣዬ አሃሃ ፡ አውቃለሁ ፡ ዞርበል ፡ አንተ ፡ ክፉ ፡ ብሩህ ፡ ቀን ፡ አያለሁ አሃሃ ፡ አውቃለሁ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጻዲቅ ፡ ነው ፡ አመሰግናለሁ አዝ፦ አውቃለሁ ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ሃሳብ ፡ እንዳለህ ፍቅር ፡ ነው ፡ አላማህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ውዴ ፍቅር ፡ ነው ፡ አላማህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ውዴ (፪x) ልዩ ፡ ነህ ፍቅር ፡ ነህ በእኔ ፡ ላይ ፡ አላማህ ፡ ልዩ ፡ ነው ልዩ ፡ ነው