Loading
Singer
በጌተ ፡ ሰማኒ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ቃቶ በቀራንዮ ፡ ላይ ፡ ከጠላት ፡ ተዋግቶ በጐቹን ፡ አድኗል ፡ ነፍሱን ፡ ለሞት ፡ ሰጥቶ እንዲህ ፡ ያለ ፡ ፍቅር ፡ ከየት ፡ ይገኛል ፡ ከቶ (፫x) መልካም ፡ እረኛ ፡ ስለ ፡ በጐቹ ነፍሱን ፡ ያኖራል ፡ በእርሱ ፡ የሚገባ በእርሱም ፡ የሚሰማራ ፡ ለዘለዓለም ፡ ይድናል ዘለዓለም ፡ ይኖራል መንጋውን ፡ ሊበትን ፡ እረኛውን ፡ መቶ ሰይጣን ፡ ቢጣጣርም ፡ እጅግ ፡ ተበራቶ ምርኮውንም ፡ መልሷል ፡ ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነስቶ ዛሬም ፡ ይደግመዋል ፡ ሕዝቦቹን ፡ ጐብኝቶ (፫x) አዎን ፡ ይሆናል ፡ መቼ ፡ ይቀራል እንጠብቃለን ፡ ለቅሷችንን ፡ በደስታ ኢየሱስ ፡ ለውጦልን ፡ ብርሃንን ፡ እናያለን (፪x) ሃዘንተኞች ፡ ስንሆን ፡ ዘወትር ፡ ደስ ፡ ይለናል ዓለም ፡ የሌላትን ፡ መድህን ፡ አግኝተናል ስለዚህም ፡ እኛ ፡ ምንም ፡ ብንገፋ ማንም ፡ አይጥለንም ፡ ከዚህ ፡ ፅኑ ፡ ተስፋ (፫x) አዎን ፡ ይሆናል ፡ መቼ ፡ ይቀራል እንጠብቃለን ፡ ለቅሷችንን ፡ በደስታ ኢየሱስ ፡ ለውጦልን ፡ ብርሃንን ፡ እናያለን (፪x) በቅርብ ፡ በሩቅ ፡ የተበተናችሁ ጌታ ፡ ቅርብ ፡ ነውና ፡ ፍፁም ፡ አይክፋችሁ የእርሱን ፡ በጐነት ፡ ለዓለም ፡ ተናግራችሁ ለጽዮን ፡ ስብሰባ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ያብቃችሁ (፫x) ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ቶሎ ፡ ቶሎ ፡ ና ናና ፡ ሰብስበን ፡ ከተበታተንበት ወደ ፡ ውድ ፡ አገራችን ፡ ጥራን ፡ አከማቸን (፪x) አዎን ፡ ይሆናል ፡ መቼ ፡ ይቀራል እንጠብቃለም ፡ ለቅሷችንን ፡ በደስታ ኢየሱስ ፡ ለውጦልን ፡ ብርሃንን ፡ እናያለን (፪x) አዎን ፡ ይሆናል ፡ (አዎን ፡ ይሆናል) መቼ ፡ ይቀራል ፡ (መቼ ፡ ይቀራል) እንጠብቃለን ፡ ለቅሷችንን ፡ በደስታ ኢየሱስ ፡ ለውጦልን ፡ ብርሃንን ፡ እናያለን (፪x)