Loading
Singer
አንዳንዴ ፡ ሲከፋኝ ፡ ግራ ፡ ሲገባኝ ፡ መሄጃው ፡ ሲጠፋኝ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ እጮሃለሁ ፡ ፊትህን ፡ እፈልጋለው ዝም ፡ አትበለኝ ፡ አትተወኝ ፡ ረዳቴ የህመሜ ፡ ፈዋሽ ፡ አንተው ፡ ነህና ፡ መድሃኒቴ (፪x) ምድረ ፡ በዳው ፡ ሲያንገላታኝ ፡ ሃሩሩ ፡ ሲያደክመኝ አይዞህ ፡ ባይ ፡ ሲጠፋ ፡ የሚቆም ፡ ከጐኔ እምባዬን ፡ አፍስሼ ፡ ተማጸንኩህ ፡ ያኔ አንተም ፡ ደረስክልኝ ፡ አልጨከንክም ፡ በእኔ "በመከራዬ ፡ ሰዓት ፡ የረዳኽኝ ፣ በጭንቄ ፡ ሰዓት ፡ የደረስክልኝ ዛሬም ፡ አልሃለሁ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አባክህን" አዝ፦ አትተወኝ ፡ እያወከው ፡ ማንነቴን አትተወኝ ፡ እያወከው ፡ እኔነቴን አትተወኝ ፡ እያወከው ፡ ደካማነቴን አትተወኝ ፡ እያወከው ፡ ውስጤን ፡ ጓዳዬን አንዳንዴ ፡ ሲከፋኝ ፡ ግራ ፡ ሲገባኝ ፡ መሄጃው ፡ ሲጠፋኝ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ ብዬ ፡ እጮሃለሁ ፡ ፊትህን ፡ እፈልጋለው ዝም ፡ አትበለኝ ፡ አትተወኝ ፡ ረዳቴ (ረዳቴ) የህመሜ ፡ ፈዋሽ ፡ አንተው ፡ ነህና ፡ መድሃኒቴ (ዝም ፡ አትበለኝ) (፪x) ከአንተ ፡ ወዴት ፡ የት ፡ እሄዳለሁ ፡ ሚስጥረኛዬ ፡ ነህ ከእስትንፋሴ ፡ ይልቅ ፡ የምትቀርበኝ ፡ ጓዴ ዛሬስ ፡ መላው ፡ ጠፋኝ ፡ መግቢያው ፡ መውጪያው ፡ ሁሉ ድምጽህን ፡ አሰማኝ ፡ ልሁን ፡ እንደቃልህ "ያኔ ፡ በልጅነቴ ፡ ወራት ፣ ድምጽህን ፡ ለመስማት ፡ የነበረኝ ፡ ጉጉትና ፡ ናፍቆት ዛሬ ፡ ግን ፡ ከውስጤ ፡ ጠፋና ፡ ወደአንተ ፡ እጮሃለሁ ፡ እባክህን (፪x)" አዝ፦ አትተወኝ ፡ እያወከው ፡ ማንነቴን አትተወኝ ፡ እያወከው ፡ እኔነቴን አትተወኝ ፡ እያወከው ፡ ደካማነቴን አትተወኝ ፡ እያወከው ፡ ውስጤን ፡ ጓዳዬን