Loading
Singer
አዝ፦ ኢየሱስን ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ አትጠራጠረው መዋሸት ፡ አያውቅም ፡ ተስፋህን ፡ ጠብቀው አይጥልህምና ፡ በመከራ ፡ ጥራው አፍህ ፡ አያመነው ፡ በልብህ ፡ አትግታው ከጠላት ፡ ፍላፃ ፡ ከሰይፍ ፡ ያድንሃል በረህብም ፡ ዘመን ፡ ከሞት ፡ ያስጥልሃል ስሙን ፡ ያስከብራል ፡ ቁም ፡ ነገርን ፡ ያውቃል ሕጻን ፡ ስላይደለ ፡ ያለውን ፡ ይፈጽማል አዝ፦ ኢየሱስን ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ አትጠራጠረው መዋሸት ፡ አያውቅም ፡ ተስፋህን ፡ ጠብቀው አይጥልህምና ፡ በመከራ ፡ ጥራው አፍህ ፡ አያመነው ፡ በልብህ ፡ አትግታው በታማንነቱ ፡ ተው ፡ ገደብ ፡ አትስጠው ለወላዋይነትህ ፡ ፅናት ፡ አትንፈገው የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር ፡ አይዋሽም የገባልህን ፡ ቃል ፡ ፈፅሞ ፡ አይክድም አዝ፦ ኢየሱስን ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ አትጠራጠረው መዋሸት ፡ አያውቅም ፡ ተስፋህን ፡ ጠብቀው አይጥልህምና ፡ በመከራ ፡ ጥራው አፍህ ፡ አያመነው ፡ በልብህ ፡ አትግታው ከእርሱ ፡ ጋር ፡ እስከሆንክ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ነው አውጥቶ ፡ እንዳይጥልህ ፡ ብቻ ፡ አትተወው አስብ ፡ ቆም ፡ ብለህ ፡ ያሳለፍከውን ፡ ዘመን ዛሬም ፡ አምነህ ፡ ጥራ ፡ ያኔ ፡ ያዳነህን አዝ፦ ኢየሱስን ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ አትጠራጠረው መዋሸት ፡ አያውቅም ፡ ተስፋህን ፡ ጠብቀው አይጥልህምና ፡ በመከራ ፡ ጥራው አፍህ ፡ አያመነው ፡ በልብህ ፡ አትግታው ስሙን ፡ እየጠራህ ፡ ስንቱን፡ አምልጠሃል ከስንቱስ ፡ አደጋ ፡ ስንት ፡ ጊዜ ፡ ድነሃል ውለታውን ፡ ሲረሱ ፡ ጌታ ፡ ቅር ፡ ይለዋል በቃሉ ፡ ብታምን ፡ ሁሉ ፡ ይቻልሃል አዝ፦ ኢየሱስን ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ አትጠራጠረው መዋሸት ፡ አያውቅም ፡ ተስፋህን ፡ ጠብቀው አይጥልህምና ፡ በመከራ ፡ ጥራው አፍህ ፡ አያመነው ፡ በልብህ ፡ አትግታው