Loading
Singer
ዓመቱ ፡ የታለ ፡ ወራትና ፡ ቀኑ እርግጥ ፡ አይኖርም ፡ ክፉ ፡ ነው ፡ ዘመኑ አንተማ ፡ ዛሬም ፡ ያው ፡ ትላንት ፡ እንደ ፡ አዩህ ስትለውጥ ፡ እንጂ ፡ ተለውጠህ ፡ አያውቁህ (፬x) አዝ፦ (አንተማ ፡ አንተማ) ፡ አትለዋወጥም (አንተማ) ፡ አትቀያየርም (አንተማ) ፡ መቼ ፡ እንደሰዉ (አንተማ) ፡ ፍቅርህ ፡ ልዩ ፡ ነዉ (፪x) ኢየሱሴ ፡ መድኃኒት ፡ ለነፍሴ ኢየሱሴ ፡ ማምለጫ ፡ ለነፍሴ (፪x) ወዳጅ ፡ ወዳጅ ፡ ወዳጅ ፡ እንዳለው ፡ ሰዉ እኔም ፡ ካንተ ፡ ጋራ ፡ እወዳጃለሁ አምላክ ፡ አምላክ ፡ አምላክ ፡ እንዳለው ፡ ሰዉ እኔም ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ መኖር ፡ እሻለሁ አዝ፦ (አንተማ ፡ አንተማ) ፡ አትለዋወጥም (አንተማ) ፡ አትቀያየርም (አንተማ) ፡ መቼ ፡ እንደሰዉ (አንተማ) ፡ ፍቅርህ ፡ ልዩ ፡ ነዉ (፪x) ኢየሱሴ ፡ መድኃኒት ፡ ለነፍሴ ኢየሱሴ ፡ ማምለጫ ፡ ለነፍሴ (፪x) ብትወደኝ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ይኸው ፡ እስከዛሬ በፍቅርህ ፡ ታስሬ ፡ አብሬ ፡ መኖሬ አመል ፡ ሆኖብኛል ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ ማለት ወዳጅ ፡ ስትሆነኝ ፡ ወረት ፡ የሌለበት (፬x) አዝ፦ (አንተማ ፡ አንተማ) ፡ አትለዋወጥም (አንተማ) ፡ አትቀያየርም (አንተማ) ፡ መቼ ፡ እንደሰዉ (አንተማ) ፡ ፍቅርህ ፡ ልዩ ፡ ነዉ (፪x) ኢየሱሴ ፡ ጠበቃ ፡ ለነፍሴ ኢየሱሴ ፡ ዋስትና ፡ ለነፍሴ ኢየሱሴ ፡ አለኝታ ፡ ለነፍሴ ኢየሱሴ ፡ መከታ ፡ ለነፍሴ (፪x)