Loading
Singer
የነበረ ፡ ያለ ፡ የሚኖር ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ በመደነቅ ፡ የሚከታተለው (፪x) የነበረው ፡ ሁሉ ፡ በነበር ፡ አለቀ የድሮ ፡ ታሪክ ፡ ነው ፡ እጅጉን ፡ የራቀ ድሮም ፡ ዛሬም ፡ ነገም ፡ ነበረ ፡ ኃያል ፡ ሆኖ በዘመናት ፡ መሃል ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው የነበረ ፡ ያለ ፡ የሚኖር ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ በመደነቅ ፡ የሚከታተለው (፪x) አዝ፦ አንተ ፡ አትለዋወጥም ፡ አሃ አንተ ፡ ኃይልህ ፡ አይቀንስም ፡ አዎ አንተ ፡ ዘመንህ ፡ አያልቅም ፡ አሃ አንተ ፡ ጉልበትህ ፡ አይዝልም ፡ አሃ (፪x) አትለዋወጥም ፡ አሃሃ (፲፮x) እኔ ፡ እኮ ፡ የሚገርመኝ ፡ ሁልጊዜ ፡ ያው ፡ መሆንህ ፡ ነው (፪x) እኔ ፡ እኮ ፡ የሚደንቀኝ ፡ ሁልጊዜ ፡ ያው ፡ መሆንህ ፡ ነው (፰x) አዝ፦ አንተ ፡ አትለዋወጥም ፡ አሃ አንተ ፡ ኃይልህ ፡ አይቀንስም ፡ አዎ አንተ ፡ ዘመንህ ፡ አያልቅም ፡ አሃ አንተ ፡ ጉልበትህ ፡ አይዝልም ፡ አሃ (፪x) አትለዋወጥም ፡ አሃሃ (፲፮x) አይተናል ፡ አዎ ፡ ኃያላን ፡ ሲያልፉ አይተናል ፡ አዎ ፡ ብርቱዎች ፡ ሲደክሙ አይተናል ፡ አዎ ፡ ቁንጅና ፡ ሲያልፍ አይተናል ፡ አዎ ፡ ውበት ፡ ሲረግፍ (፪x) አዝ፦ አንተ ፡ አትለዋወጥም ፡ አሃ አንተ ፡ ኃይልህ ፡ አይቀንስም ፡ አዎ አንተ ፡ ዘመንህ ፡ አያልቅም ፡ አሃ አንተ ፡ ጉልበትህ ፡ አይዝልም ፡ አሃ (፪x) አትለዋወጥም ፡ አሃሃ (፲፮x) እነ ፡ ኃያላን ፡ እነ ፡ አለቆች እነ ፡ ነገሥታት ፡ እነ ፡ አልሞት ፡ ባዮች አንድ ፡ በአንድ ፡ ሁሉም ፡ ሁሉም ፡ አለፉ እያየናቸው ፡ ከምድር ፡ ላይ ፡ ጠፉ (፪x) አንተ ፡ ግን ፡ አትለዋወጥም ፡ አሃ አምላኬ ፡ አትለዋወጥም ፡ አሃ አምላክህ ፡ አይለዋወጥም ፡ አሃ አምላክሽ ፡ አይለዋወጥም ፡ አሃ እርሱ ፡ እኮ ፡ አይለዋወጥም ፡ አሃ አምላኬ ፡ አይለዋወጥም ፡ አሃ አምላክህ ፡ አይለዋወጥም ፡ አሃ አምላክሽ ፡ አይለዋወጥም ፡ አሃ አትለዋወጥም ፡ አሃሃ (፲፮x) ትልቅ ፡ ነህ ፡ ሰፊ ፡ ነህ ፡ ጥልቅ ፡ ነህ ፡ ረቂቅ (፪x) በዓይኔ ፡ በብረቱ ፡ አይቻለሁ ፡ አሃ ትልቅነትህን ፡ አይቻለሁ ፡ አሃ የማይሆነው ፡ ሲሆን ፡ አይቻለሁ ፡ አሃ ያለቀ ፡ ሲጀምር ፡ አይቻለሁ ፡ አሃ (፪x) ስለዚህ/እኔማ ፡ አምልክሃለሁ ወገቤን ፡ ታጥቄ ፡ አምልክሃለሁ ልክህን ፡ አውቄ ፡ አምልክሃለሁ ልክህን ፡ አውቄ (፬x)