Loading
Singer
አዝ፦ አጠገቤ ፡ ሆኗል ፡ ጌታ (፬x) ከእንግዲህ ፡ የቱ ፡ ያስፈራኛል እግዚአብሔር ፡ ጋሻ ፡ ሆኖልኛል ከእንግዲህ ፡ የቱ ፡ ያሰጋኛል አባቴ ፡ ቅጥር ፡ ሆኖልኛል በብቸኝነቴ ፡ አይዞህ ፡ ባይ ፡ ማጣቴ ትዝ ፡ ሲለኝ (፪x) የለቅሶ ፡ እንጉርጉሮ ፡ ሲሰማ ፡ ከቤቴ ትዝ ፡ ሲለኝ (፪x) የእኔስ ፡ ነገር ፡ የእኔስ በዓይን ፡ አይቶ ፡ ሳለቅስ ያልራቀኝ ፡ ንጉሥ የልጅነት ፡ ጓደኛ ስሆን ፡ ያኔ ፡ ብቸኛ ኢየሱስ ፡ አለኛ አዝ፦ አጠገቤ ፡ ሆኗል ፡ ጌታ (፬x) ከእንግዲህ ፡ የቱ ፡ ያስፈራኛል እግዚአብሔር ፡ ጋሻ ፡ ሆኖልኛል ከእንግዲህ ፡ የቱ ፡ ያሰጋኛል አባቴ ፡ ቅጥር ፡ ሆኖልኛል የቅርብ ፡ ወንድሞቼ ፡ ሁሉ ፡ የከዱኝ ትዝ ፡ ሲለኝ (፪x) ያለርህራሄ ፡ ጉድጓድ ፡ የጣሉኝ ትዝ ፡ ሲለኝ (፪x) የእኔስ ፡ ነገር ፡ የእኔስ በዓይን ፡ አይቶ ፡ ሳለቅስ ያልራቀኝ ፡ ንጉሥ የልጅነት ፡ ጓደኛ ስሆን ፡ ያኔ ፡ ብቸኛ ኢየሱስ ፡ አለኛ አዝ፦ አጠገቤ ፡ ሆኗል ፡ ጌታ (፬x) ከእንግዲህ ፡ የቱ ፡ ያስፈራኛል እግዚአብሔር ፡ ጋሻ ፡ ሆኖልኛል ከእንግዲህ ፡ የቱ ፡ ያሰጋኛል አባቴ ፡ ቅጥር ፡ ሆኖልኛል ለእኔስ ፡ አይዞህ ፡ ብለው ፡ የሚያጽናኑኝ ወዳጆቼም ፡ ችላ ፡ ቢሉኝ የቅርቦቼም ፡ ችላ ፡ ቢሉኝ እናት ፡ ልጇን ፡ እንኳን ፡ ብትረሳ ልጄ ፡ ካለ ፡ የማይከዳ ጌታ ፡ አለ ፡ ከእኔስ ፡ ጋራ (፪x)