Loading
ሀ ፡ ሁ ፡ ጌታ (፪x) አጠገቤ ፡ ካለው ፡ ሰው ፡ ይልቅ እርሱ ፡ ይቀርበኛል መገኘቱ ፡ ህልውናው ፡ ይታወቀኛል (፪x) ከውንድም ፡ ይልቅ ፡ ይጠጋጋኛል ከእስትንፋሴ ፡ ይልቅ ፡ ይቀርበኛል ጌታ ፣ ጌታ ፣ ጌታ ፣ ጌታ ፣ ጌታ (፬x) በልቤ ፡ ያለህ ፡ ትልቅ ፡ ቦታ ዘውትር ፡ ላክብርህ ፡ ሁሌ ፡ ጥዋት ፡ ማታ ለእኔ ፡ ለእኔ ፡ አጠገቤ ፡ ካለው ፡ ሰው ከሚነካኝ ፡ ከምነካው ፡ ከሚዳስሰኝ ፡ ከምዳስሰው በዓይኑ ፡ ከሚያየኝ ፡ በዓይኔ ፡ ከማየው እርሱ ፡ ለእኔ (፫x) ፡ ቅርቤ ፡ ነው በገባሁበት ፡ አብሮ ፡ ይገባል በሄድኩበት ፡ አብሮ ፡ ይሄዳል እንደ ፡ እርሱ ፡ ያለ ፡ ወዳጅ ታዲያ ፡ ከየት ፡ ይገኛል አያያያያያያያ እንደ ፡ እርሱ ፡ ያለ ፡ ወዳጅ ታዲያ ፡ ከየት ፡ ይገኛል (፪x) ሥም ፡ ሰማዬ ፡ ምድርን ፡ ሞልቷል እንደ ፡ እርሱ ፡ ያለ ፡ ከየት ፡ ይገኛል መኖሩን ፡ ደስ ፡ በሚለው ፡ መንፈሱ ፡ ይገልጥልኛል (፪x) አጠገቤ ፡ ካለው ፡ ሰው ፡ ይልቅ እርሱ ፡ ይቀርበኛል (፪x) ስፍራን ፡ አይመርጥም ጊዜን ፡ አይመርጥም (፬x) ሀ ፡ ሁ ፡ ጌታ (፪x) አጠገቤ ፡ ካለው ፡ ሰው ፡ ይልቅ ፡ እርሱ ፡ ይቀርበኛል መገኘቱ ፡ ህልውናው ፡ ይታወቀኛል (፪x) ከውንድም ፡ ይልቅ ፡ ይጠጋጋኛል ከእስትንፋሴ ፡ ይልቅ ፡ ይቀርበኛል ጌታ ፣ ጌታ ፣ ጌታ ፣ ጌታ ፣ ጌታ (፬x) በልቤ ፡ ያለህ ፡ ትልቅ ፡ ቦታ ዘውትር ፡ ላክብርህ ፡ ሁሌ ፡ ጥዋት ፡ ማታ ታማኝ ፡ ወገኔ ፡ ያለኝ ፡ በጐኔ ታማኝ ፡ ወዳጄ ፡ ያለኝ ፡ በእጄ በፍቅሩ ፡ ውበት ፡ ሁሉ ፡ የማትለየኝ ታላቁ ፡ ጌታ ፡ የምትወደኝ ታላቁ ፡ ኢየሱስ ፡ የምትመራኝ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.