Loading
Singer
ጥቂት ፡ ጊዜ ፡ አለፈ ፡ ከተናገርካቸው አብርሃምና ፡ ሳራን ፡ ተስፋ ፡ ፈተናቸው ከዚህ ፡ የተነሳ ፡ እርምጃን ፡ ወሰዱ አንተንም ፡ ቀደሙ ፡ እስማኤልን ፡ ወለዱ ግን ፡ አንተ ፡ ጌታችን ፡ ስለተስፋህ ፡ ብለህ ይስሐቅን ፡ አምጥተህ ፡ ቃልህን ፡ ፈጸምህ (፪x) አዝ፦ አትቸኩልም ፡ አንተ ፡ ደግሞም ፡ አትዘገይም ቀስ ፡ እያልክ ፡ ብትሄድ ፡ ማንም ፡ አይቀድምህም ነገርን ፡ በሙሉ ፡ በጊዜው ፡ ውብ ፡ አድርገህ በድንቅ ፡ በተዓምራት ፡ ታበጃጀዋለህ ክብርህን ፡ ትገልጻልህ ወንድሞቹ ፡ ሲሰግዱ ፡ ዮሴፍ ፡ ህልምን ፡ አየ ግን ፡ የኖረው ፡ ኑሮ ፡ ከዚህ ፡ የተለየ ቃልህ ፡ እስኪመጣለት ፡ እርሱም ፡ ተፈተነ በእርኩሰት ፡ በኃጢአት ፡ ላይ ፡ ሁሌ ፡ እየጨከነ የሚጐበኝበት ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቀን ፡ መጣ ከእዛ ፡ ጉስቁልናው ፡ ከመከራ ፡ ወጣ (፪x) አዝ፦ አትቸኩልም ፡ አንተ ፡ ደግሞም ፡ አትዘገይም ቀስ ፡ እያልክ ፡ ብትሄድ ፡ ማንም ፡ አይቀድምህም ነገርን ፡ በሙሉ ፡ በጊዜው ፡ ውብ ፡ አድርገህ በድንቅ ፡ በተዓምራት ፡ ታበጃጀዋለህ ክብርህን ፡ ትገልጻልህ ሃና ፡ መካኗ ፡ ሴት ፡ ብዙ ፡ አለቀሰች በወገኖች ፡ ሳይቀር ፡ እየተነቀፈች እርሷም ፡ እንደ ፡ ሰዎች ፡ ዘመኗ ፡ ደረሰ ልቧ ፡ በአንተ ፡ ጸና ፡ ታሪኳም ፡ ታደሰ አቤት ፡ የእግዚአብሔር ፡ ስራው ፡ ያስደንቃል የምስኪኑን ፡ እንባ ፡ በጊዜው ፡ ያደርቃል (፪x) አዝ፦ አትቸኩልም ፡ አንተ ፡ ደግሞም ፡ አትዘገይም ቀስ ፡ እያልክ ፡ ብትሄድ ፡ ማንም ፡ አይቀድምህም ነገርን ፡ በሙሉ ፡ በጊዜው ፡ ውብ ፡ አድርገህ በድንቅ ፡ በተዓምራት ፡ ታበጃጀዋለህ ክብርህን ፡ ትገልጻልህ በጣም ፡ የምትወደው ፡ አልዓዛር ፡ ታሟል የሚል ፡ ድምጽ ፡ ከሰማ ፡ አራት ፡ ቀን ፡ ሆኖታል የሞተውን ፡ ሊያስነሳ ፡ እንባቸውን ፡ ሊያብስ በራሱ ፡ ጊዜ ፡ መጣ ፡ ጌታችን ፡ ኢየሱስ ዛሬም ፡ ብንጠብቀው ፡ በመጠበቂያችን እግዚአብሔር ፡ ቅርብ ፡ ነው ፡ ክብሩን ፡ ሊገልጽልን (፪x) አዝ፦ አትቸኩልም ፡ አንተ ፡ ደግሞም ፡ አትዘገይም ቀስ ፡ እያልክ ፡ ብትሄድ ፡ ማንም ፡ አይቀድምህም ነገርን ፡ በሙሉ ፡ በጊዜው ፡ ውብ ፡ አድርገህ በድንቅ ፡ በተዓምራት ፡ ታበጃጀዋለህ ክብርህን ፡ ትገልጻልህ