Loading
Singer
በኃይለኛው ፡ ላይ ፡ ብርቱ ፡ ኃይለኛ በሚዳኘው ፡ ላይ ፡ ሲሰየም ፡ ዳኛ በዓለቃው ፡ ላይ ፡ አለ ፡ አለቃ የሰው ፡ ሹመቱ ፡ ልኩ ፡ ሲያበቃ ከፍ ፡ ካሉት ፡ በላይ ፡ ከፍ ፡ ብለህ ፡ በዙፋንህ ፡ ላይ የከበረ ፡ የታወቀ ፡ የገነነ ፡ ከሁሉ ፡ የላቀ ከሥም ፡ ሁሉ ፡ ሥመኛ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ዝነኛ የለህ ፡ አቻ ፡ እኩያ ፡ የለህ ፡ ምትክ ፡ አምሳያ አዝ፦ አታይም ፡ ወደላይ ፡ የለህም ፡ የበላይ የሁሉ ፡ አለቃ ፡ ነህ ፡ የሁሉ ፡ ጌታ አታይም ፡ ወደላይ ፡ የለህም ፡ የበላይ የሁሉ ፡ ፈጣሪ ፡ ነህ ፡ የሁሉም ፡ መሪ ከላይ ፡ የመጣው ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው እግዚአብሔር ፡ ካለልክ ፡ ከፍ ፡ ያደረገው እኛ ፡ ዝቅ ፡ ልንል ፡ እርሱ ፡ ግን ፡ ሊልቅ ፡ ነው የተገባው ፡ ነዉ ፡ ከሁሉ ፡ ሊበልጥ (፪x) ኧረ ፡ ይህንን ፡ ጌታ ሊሽር ፡ ማንስ ፡ ሊረታ ሹመቱ ፡ ዙፋኑ ፡ ጽኑ ገደብ ፡ የለው ፡ ስልጣኑ አዝ፦ አታይም ፡ ወደላይ ፡ የለህም ፡ የበላይ የሁሉ ፡ አለቃ ፡ ነህ ፡ የሁሉ ፡ ጌታ አታይም ፡ ወደላይ ፡ የለህም ፡ የበላይ የሁሉ ፡ ፈጣሪ ፡ ነህ ፡ የሁሉ ፡ መሪ በሃይለኛው ፡ ላይ ፡ ብርቱ ፡ ሃይለእኛ በሚዳኘው ፡ ላይ ፡ ሲሰየም ፡ ዳኛ በዓለቃው ፡ ላይ ፡ አለ ፡ አለቃ የሰው ፡ ሹመቱ ፡ ልኩ ፡ ሲያበቃ ከፍ ፡ ካሉት ፡ በላይ ፡ ከፍ ፡ ብለህ ፡ በዙፋንህ ፡ ላይ የከበረ ፡ የታወቀ ፡ የገነነ ፡ ከሁሉ ፡ የላቀ ከስም ፡ ሁሉ ፡ ስመኛ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ዝነኛ የለህ ፡ አቻ ፡ እኩያ ፡ የለህ ፡ ምትክ ፡ አምሳያ አዝ፦ አታይም ፡ ወደላይ ፡ የለህም ፡ የበላይ የሁሉ ፡ አለቃ ፡ ነህ ፡ የሁሉ ፡ ጌታ አታይም ፡ ወደላይ ፡ የለህም ፡ የበላይ የሁሉ ፡ ፈጣሪ ፡ ነህ ፡ የሁሉ ፡ መሪ በማስተዋል ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያለ እራሱን ፡ አዋርዶ ፡ የከበረ በሰማይም ፡ በምድርም ፡ ክምድር ፡ በታችም ፡ የገነነ ምላስ ፡ ሁሉ ፡ ይመሰክራል ፡ ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ይንበረከካል ለእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ለኢየሱስ ፡ አለቅነት ፡ ተገብቶታል አዝ፦ አታይም ፡ ወደላይ ፡ የለህም ፡ የበላይ የሁሉ ፡ አለቃ ፡ ነህ ፡ የሁሉ ፡ ጌታ አታይም ፡ ወደላይ ፡ የለህም ፡ የበላይ የሁሉ ፡ ፈጣሪ ፡ ነህ ፡ የሁሉ ፡ መሪ