Loading
Singer
አስተምረኝ ፡ ጌታዪ ፡ ሆይ ፡ አስተካክላት ፡ ሕይወቴን መንገዴን ፡ ሁሉ ፡ ስራመድ ፡ አንተ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ሁን (፪x) ክፉና ፡ ደጉን ፡ ለይቶ ፡ ሳያውቀው አስተምረኝ ፡ አለ ፡ ሌላው ፡ እንዳይነካው እንካ ፡ ተረከባት ፡ ሕይወቴን ፡ አደራ በቤትህ ፡ አንድኖር ፡ አንተን ፡ እንድፈራ ልጅነቴን/ጉብዝናዬን ፡ ንገሥበት እስከ ፡ እርጅና ፡ እስከ ፡ ሽበት ክበርብኝ ፡ ለየኝና ታናሹን ፡ የአንተን ፡ ብላቴና (፪x) መልካም ፡ አባት ፡ መቼ ፡ ይጥላል(፪x) ቃልኪዳኑን ፡ ይጠብቃል (፪x) ታማኝ ፡ ነው ፡ አደራ ፡ ላለው ፡ በመንገዱ ፡ ለተከተለው ያቆመዋል ፡ በቤቱ ፡ ተክሎ ፡ ያጸናዋል ፡ ልጄ ፡ ነህ ፡ ብሎ (፪x) አስተምረኝ ፡ ጌታዪ ፡ ሆይ ፡ አስተካክላት ፡ ሕይወቴን መንገዴን ፡ ሁሉ ፡ ስራመድ ፡ አንተ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ሁን (፪x) (አስታውሳለው) ፡ ወንድሞቼን ፡ እህቶቼን ፡ የጨቅላነት ፡ ጓደኞቼን (አስታውሳለው) ፡ ኧረ ፡ አይጠፋም ፡ ከአዕምሮዬ ፡ የልጅነት ፡ ትዝታዬ (አስታውሳለው) ፡ ተሰብስበን ፡ ስንዘምር ፡ አንዱ ፡ ለአንዱ ፡ ያለው ፡ ፍቅር (አስታውሳለው) ፡ ክፋት ፡ የለ ፡ መሀላችን ፡ ያ ፡ ቅን ፡ ዘመን ፡ አቤት ፡ ሲያምር