Loading
Singer
እንደ ፡ ጀግና ፡ ወንድ/ሰው ፡ እንደ ፡ እልፍ ፡ ገዳይ እንጐራደዳለሁ/ፎክርበታለሁ ፡ በጠላቴ ፡ ላይ ተረታው ፡ ሳይል ፡ እጁን ፡ ዘርግቶ ማጥቃት ፡ መዋጋትን ፡ አልተውም ፡ ከቶ (፪x) ተወርውሮ ፡ ከቶ ፡ የማይስተው የጌታዬ ፡ የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ነው ደጋግሜ ፡ እርሱን ፡ ጠራዋለሁ በጠላቴ ፡ ላይ ፡ ከፍ ፡ እላለሁ ሲቀረቀር ፡ በግንባሩ ፡ ላይ በእጄ ፡ ያለው ፡ የያዝኩት ፡ ድንጋይ ላዩ ፡ ቆሜ ፡ አንገቱን ፡ ቆርጥና አውጃለሁ ፡ የጌታዬን ፡ ዝና አዝ፦ አሸናፊ ፡ ነኝ ፡ የጌታ/የኢየሱስ ፡ ሆኜ አፍሬ ፡ አላውቅም ፡ እርሱን ፡ ታምኜ (፪x) እኔም ፡ እንደ ፡ ዳዊት ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሰው በሕዝቤ ፡ ጠላት ፡ ላይ ፡ ሥምህን ፡ ላንሳው በሰልፉ ፡ ሜዳ ፡ ላይ ፡ ወደ ፡ መሃል ፡ ልግባ ጠላትን ፡ ዘርሬ ፡ ላፍስስ ፡ የደስታ ፡ እንባ እኔ ፡ እያየሁ ፡ ጐልያድ ፡ በእስራኤል ፡ ላይ ፡ አይፎክርም እኔ ፡ እያለሁ ፡ ጠላት ፡ በሕዝቤ/በምድሬ ፡ ላይ ፡ አይዘብትም (፪x) የአንበሳን ፡ ደቦል ፡ የሚገነጥል ግዙፉን ፡ ሠራዊት ፡ ሰባብሮ ፡ የሚጥል የአምላኬ ፡ ክብሩ ፡ ነው ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ከቶ ፡ እንደምን ፡ ልስጋ ፡ እንዴትስ ፡ ልፍራ (፪x) ፍልስጤሞች ፡ ያገኙኝ ፡ መስሏቸው በመንደሩ ፡ ሞላ ፡ ዕልልታቸው በጠንካራዉ ፡ ገመድ ፡ አስረውኛለው በእነሱ ፡ ቤት ፡ ማን ፡ ያስጥለኛል ወረደብኝ ፡ መንፈሱ ፡ የጌታ እስራቴም ፡ ላላ ፡ ተፈታታ በእጄ ፡ ገቡ ፡ ጠፉ ፡ ጠላቶቼ ገመድኳቸው ፡ መጥቼ ፡ ፈትቼ አዝ፦ አሸናፊ ፡ ነኝ ፡ የጌታ/የኢየሱስ ፡ ሆኜ አፍሬ ፡ አላውቅም ፡ እርሱን ፡ ታምኜ (፪x) አሞት ፡ ይሆናል ፡ ወይ ፡ መንገድ ፡ ሄዶ አንቀላፍቶም ፡ ይሁን ፡ ይህ ፡ ከንቱ ፡ ባዶ በአሕዛብ ፡ አምላክ ፡ እሳለቃለሁ በማንነቱም ፡ ላይ ፡ እዘብታለሁ (፪x) አምላክ ፡ ሳይሆን ፡ አምላክ ፡ ነኝ ፡ ባዩን መዘዝኩበት ፡ ስለታም ፡ ሰይፌን ነብያቱን ፡ በሙሉ ፡ አረድኳቸው እስቲ ፡ ያድን ፡ ይምጣ ፡ አምላካቸው የሚመልስ ፡ በእሳት ፡ ተገልጦ የአሕዛብን ፡ አምላክ ፡ አስደንግጦ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ሥሙም ፡ እግዚአብሔር ከፍ ፡ ብሎ ፡ ተከብሮ ፡ የሚኖር አዝ፦ አሸናፊ ፡ ነኝ ፡ የጌታ/የኢየሱስ ፡ ሆኜ አፍሬ ፡ አላውቅም ፡ እርሱን ፡ ታምኜ (፪x) እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሰው ፡ እንደ ፡ ኤልያስ በምድር ፡ ኢትዮጵያ ፡ ላይ ፡ ሥምህ ፡ እንዲነግስ ከበአል ፡ ነቢያት ፡ እወራረዳለሁ ክብርህን ፡ ስትገልጥ ፡ እረታቸዋለሁ እኔ ፡ እያየሁ ፡ በአል ፡ አምላክ ፡ ተብሎ ፡ አይመለክም እኔ ፡ እያለሁ ፡ የጌታዬ/የኢየሱስ ፡ ክብር ፡ አይሸፈንም (፪x) አንተ ፡ እያለህ ፡ እውነት ፡ እንጂ ፡ ውሸት ፡ አይሰበክም አንተ ፡ እያለህ ፡ ወንጌል ፡ እንጂ ፡ ክደት ፡ አይነገርም አንቺ ፡ እያለሽ ፡ እውነት ፡ እንጂ ፡ ውሸት ፡ አይሰበክም አንቺ ፡ እያለሽ ፡ ወንጌል ፡ እንጂ ፡ ክደት ፡ አይነገርም